የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 7 ቤተክርስቲያኖች ተቃጠሉ | በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደረሰ

February 10, 2019

ከአዲስ አበባ 239 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 7 ቤተክርስቲያኖች ሲቃጠሉ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ታወቀ:: እንዲሁም ሕዝብ ማመላለሻ ባጃጆች እና የቀይ መስቀል ታርጋ የለጠፈ ሞተር ሳይክል በግጭቱ ወድሟል::

https://www.youtube.com/watch?v=mk2qgm5fFUY

በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የተነሳ እነዚህ 7 ቤተክርስቲያን ሊቃጠሉ መቻላቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ገልጿል;; የዞኑ የኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድ ኑር እንደገለጹት ጉዳቱ የደረሰው “በዱራሜ አካባቢ መስጊዶች ላይ ጥቃት ደርሷል” በሚል በተሰራጨ የተሳሳተ የማህበራዊ ድረ-ገጾች መረጃ አማካኝነት ነው። በዚህ የተነሳም እስከ ትናንት ቀትር ድረስ በከተማዋ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያኖችና የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ በተደራጁ ህገ-ወጥ ወጣቶች ጥቃት መፈጸሙን የተናገሩት አቶ መሐመድ ኑር “ጥቃቱ ቅጥር ግቢያቸውን ከማፍረስና ከማቃጠል ጀምሮ የመገልገያ ቁሳቁሶችን እስከ መሰባበር የደረሰ ነበር” ብለዋል::

በዚህ ጥቃት ከአስር የማያንሱ ዜጎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሲታወቅ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተረድተናል:: በአካባቢው የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያናቱን ለማጥፋት ርብርብ አድርገዋል:: ቤተክርስቲያናቱ በሚቃጠሉበት ወቅት ለማጥፋት ከሄዱ የ እሳት አደጋ ሰራተኞች መካከል አንዱ መቁሰሉን የተናገሩት አቶ መሕመድ
ግጭቱን ለመቆጣጠር ፖሊስና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ማረጋጋታቸውንና አጥፊዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩን ገልጸዋል::
አቶ መሐመድ ድርጊቱን በአካባቢው የተከሰተው ግጭትና ቤተክርስቲያን ማቃጠል የከተማውን ሕዝብ የማይወክልና ጥቂት ግለሰቦች ሁከት ለመፍጠርና የኅብረተሰቡን አብሮ የመኖር ባህል ውስጥ ጥርጣሬ ለመክተት ነው ብለውታል::

Previous Story

የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማነጋገር እፈልጋለሁ አለች | Video

Next Story

በባህርዳር ስታዲየም ኳስ ለማየት የገቡ ተመልካቾች “መከላከያ ከጎንደር ይውጣ” ሲሉ መፈክር አሰሙ | ጀነራል አሳምነው ጽጌ በከሚሴ አካባቢ ከጎንደሩ ጋር በተመሳሳይ ወቅትና በተቀናጀ መንገድ ጥቃት ተፈጽሞ ያከሸፈው መከላከያው ነው አሉ

Go toTop