በሁለት ዓመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ታቅዶና በ258 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የጊዳቦ መስኖ ልማትና ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከስምንት ዓመታት መጓተት በኋላ በ1.66 ቢሊዮን ብር wettobet ግንባታው ሳይጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ተመረቀ:: በምርቃቱ ላይ የተገኙት ዶ/ር አብይ አሕመድ የጊዳቦ ግድብ ፕሮጀክት የምእራብ ጉጂና ሲዳማ ዞን ህዝቦችን ያቀራረበ ነው ሲሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ የሚታየውን አላስፈላጊ ክርክርና ንትርክ አቁመን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው እንደ ጊዳቦ ባሉ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት እናድርግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=FBF1dd_4gao&t=93s
የኢትዮጵያ መንግስት ለግብርናና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማልማት በሰጠው ትኩረት መሰረት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን የሚያቀራርቡ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ይቀረጻሉ:: ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከመጠየቅ አልፈው የተገኙ ድሎች ላይ በመንተራስ ለአገራቸው እድገት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ይገባል ሲሉ ጥሪ ያቀረቡት ዶ/ር አብይ የጊዳቦ የመስኖ ፕሮጀክቱ ከልማቱ ባሻገር የሲዳማና የጉጂ ህዝብን አቀራርቦ የሚያስተሳስር ነው ብለውታል::
“ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ ከዲዛይን እስከ ግንባታ በኢትዮጵያዊያን መሰራቱም ለሃገር ታላቅ ኩራት ነው” ያሉት ዶ/ር አብይ “ዘመናዊ መስኖን በማስፋት ሃገራችን ያላትን የውሃና የመሬት ሀብት በመጠቀም ከመቀየር የበለጠ አመራጭ የላትም:: ይህን በመረዳት ለእድገትና ለመለወጥ ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል” ሲሉ ጥሪ አቀርበዋል::
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂና በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞንን በማስተሳሰር ጊዳቦ ወንዝ ላይ የተገነባው ይህ ዘመናዊ የመስኖ ግድብ; በ4.3 ኪሎ ሜትር ስፋት መሬት ላይ ውሃ እንዲይዝ ተደርጎ መገንባቱንና 1ሺህ 2 መቶ ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሰው ሰራሽ ሀይቅ እንዳለው በምርቃቱ ላይ ተገልጿል::
በምርቃቱ ላይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተገኝተው የደቡብን እና የኦሮሞን ሕዝብ ይበልጥ ግድቡ እንደሚያቀራርብ በመግለጽ ንግግር አድርገዋል:: ዕንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳም የተገኙ ሲሆን ባሰሙት ንግግርም “በተለይም አቶ ለማ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ጊዜ የሚታየውን አላስፈላጊ ክርክርና ንትርክ በመተው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው እንደ ጊዳቦ ባሉ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ትኩረት ልናደርግ ይገባል::” ብለዋል::
ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ ከተመረቁት መካከል የርብ መስኖ ፕሮጀክት፣ የባህርዳር ዩንቨርስቲ ሆስፒታልና የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የሚጠቀሱ ይጠቀሳሉ:: ዛሬ ጊዳቦ ሶመረቅ ከግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ባሻገር ቀጣይ ስራ የሆነው የመስኖ ካናል ዝርጋታና ቀሪ የልማት አውታሮች ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ በሺዎች የሚቆጠሩት የሁለቱ ክልል ወጣቶችና አርሶ አደሮች ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ርብርብ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡
ከግዱ ምረቃ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ; አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ ከጉጂ አባ ገዳዎችና ከዞኑ ነዋሪዎች ተወያይተዋል:: በዚህ ወቀት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የአካባቢው ማህበረሰብ መሰረታዊ ልማትን ለማምጣት ሰላም ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩጽህፈት ቤት አስታውቀዋል:: ከውይይቱ በኋላም የአካባቢው ነዋሪም ለመሪዎቹ ሽልማት ማበርከቱንም ሰምተናል::