በሳዑዲ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ የሚደረገውን ግፍ ለማስቋም በጋራ እንቁም

November 13, 2013

ህዳር ፫ ቀን ፳፻፮

November 11, 2013

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክርቤት ቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች እየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ አጢኗል። ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለጠ ከጎናቸው እንደሚቆምም አረጋግጧል።

ምክርቤቱ ይህ ህገ ወጥ ተግባር ባሰቸኳይ እንዲቆም ለማድረግ አለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ዘመቻ እንዲካሄድ የወሰነ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የሸንጎው አባላትና ደጋፊዎች ሰላማዊ ስልፍ እንዲያስተባብሩና እንዲያካሂዱ፣ ስልፍ ለማካሄድ የማስተባበር ስራ በተጀመረባቸውቦታዎችም ከሌሎች ጋር በመተጋገዝ የሳዑዲ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች የሚያካሂዱትን ህገወጥ ተግባር ባስቸኳይ እንዲያቆሙ ግፊት እንዲያደርጉ፤ ከሳዑዲ መንግስት ዲፕሎማቶች ጋር  በግንባር በመነጋገር የኢትዮጽያውያን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የታሰሩት ባስቸኳይ እንዲፈቱና የተገደሉና ስቃይ የደረሰባቸውንም በተመለከተ አስፈላጊው ማጣራትና  ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እንዲጠይቁአስቸካይ መመሪያ ስጥቷል።

በተጨማሪም፣ የሽንጎው አባል ድርጅቶችና ደጋፊዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ይህንኑ ጉዳይ አጽንዖት ሰጥተው  ለዓለምአቀፉ የመብት ተሟጋቾችና መንግሥታት በማስታወቅ በሳዑዲ መንግሥት ላይ የየራሳቸውን ግፊት እንዲያደርጉ እንዲጠይቁ ተጨማሪ መመሪያ ሰጥቷል።

በወገኖቻችን ላይ ሳዑዲ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ግፍ ለማስቆም ሁላችንም የፖለቲካ ልዩነትን ወደጎን አድርገን ባስቸኳይ እንድንተባበር የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ጥሪውን ያቀርባለን።

ለወገን አድኑ ጥሪ በጋራ እንቁም፡

 

[gview file=”https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2013/11/saudi-appeal-shengo.pdf”]


Previous Story

ጃኪ ጎሲ በሳዑዲ ላሉ ወገኖቻችን መታሰቢያ ነጠላ ዜማ ለቀቀ

Next Story

የእህታችን አሳዛኝ የቪድዮ መልዕክት ከሳዑዲ አረቢያ

Go toTop