ታዋቂዋ እንስት ፖለቲከኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ በሚቀጥለው ሳምንት ወኢትዮጵያ እንደምትገባ ታወቀ:: ለረዥም ዓመታት በ እስር ላይ የቆየችው የቀድሞው በስድስት ኪሎና ፈረንሳይ አካባቢ የፓርላማ ተወዳዳሪና የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ሃገር ቤት የምትገባው በዶ/ር አብይ አህመድ ግብዣ መሆኑ ታውቋል::
በአቶ መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ በነበረችበት ወቅት የህጉን ክፍተት ተመልክታ የሕወሓቱን ባለስልጣን ስዬ አብርሃን ከፍርድ ቤት እንዲለቀቅ በመወሰን ባሳየችው ድፍረት የምትታወቀው ብርቱካን የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣ የአንድነት ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር በመሆን ለእስር በመዳረግ ከፍተኛ መስዋትነት ከፍላለች::
ከ እስር ከወጣች በኋላ በአሜሪካ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪዋን የተቀበለችው ብርቱካን ከፖለቲካው ዓለም ራሷን አርቃ ሰንብታለች:: ብርቱካን በዶ/ር አብይ አህመድ ግብዣ የፊታችን ጥቅምት 28/2011 ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስታ፤ ሐሙስ ጥቅምት 29/2011 ኢትዮጵያ እንደምትገባ ምንጮች ተናግረዋል::
ብርቱካን የአንዲት ሴት ልጅ እናት መሆኗ ይታወቃል::
https://www.youtube.com/watch?v=92rppGAN2Dk