ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ህዳር 1 ቀን 2006 ፕሮግራም
<...ዜጎች ሲደበደቡ ፣ሲደፈሩ፣ሲገደሉ፣ሲያብዱ ካልደረሱ ከሶስት ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪ ህጻናት የሚማሩበት ት/ቤት ሲዘጋ ዝም ሲሉ ለተራቡ ዜጎቻችን ለችግር ቀን ተብሎ ከራሱ ከስደተኛው የተዋጣውን አራት ሚሊዮን ብር ሲያግዱ ተቆርቋሪ መሆን ካልቻሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተብለው ምንድነው የሚሰሩት? ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ ነው? ...በተለያየ ቦታ ያለውም ኢትዮጵያዊ የሳውዲ መንግስት ሕግን እንዲያከብር በህግ አግባብ እንዲሰራ ድምጹንማሰማት አለበት...>
ጋዜጠኛ ነብዪ ሲራክ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት
<<...ማን ይሰማናል የኤምባሲያችን ስልክ አይነሳም። ወገኖቻችን ይህን እያዩ ዝም ማለት የለባቸውም...ምነው እዛው አገራችን ረሃብ ቢገለን ይሻላል>>የሃያ ዓመቱዋ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ከሳውዲ
<<...አስራ ሰባት ዓመቴ ነው። ሃያ አምስት ብዬ ነው ፓስፖርቴን ያወጣሁት።...>>
የ17 ዓመቷ ልጅ በጅዳ ለህብር ከተናገረችው ስለ በደሏ ለመናገር ሰዎቹን ፈርታ ቀጠሮ ሰጠችን በቀጠሮ ፈልገን …(አዳምጧት)
ሁለት ኩላሊቷ አልሰራ በማለቱ በጤና መታወክ ላይ ያለችው ኢትዮጵያዊ የልጆች እናት ኢንሹራንስ አልባ መሆን እና የኦባማ ኬር ያካትታት ይሆን(የዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ማብራሪያና ከበሽተኛዋ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
የቻይና የእጅ አዙር የኢኮኖሚ ቅኝ ግዛት(ልዩ ዘገባ)
(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)
ዜናዎቻችን
– በሳዑዲ አረቢያ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከአስር በላይ ደረሰ
– ዕውቁ የጸረ አፓርታይድ አክቲቪስትና ጋዜጠኛ እነ እስክንድር እንዲፈቱ በአዲስ አበባ ጠየቁ
– በላምባዱሳ በባህር ላይ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተጠያቂ የተባለ ተጠርጣሪ ተያዘ
– በሶማሊያ የኢትዮጵያና የኬኒያ ወታደሮች ግንባር መፍጠር ኬኒያውያኑ ላይ ስጋት ደቀነ
– የናይጄሪያ ቡድን ከኢትዮጵያ ከመጫወቱ በፊት ጉርሻ ጠየቀ
– ፊፋ ከጋምቢያና ኤርትራ ዳኛ መደበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን