የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) በአገራችን ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለው አምባገነን አገዛዝ ሕዝባችንን ከዕለት ወደ ዕለት ለከፋ ስቃይ እየዳረገው እንደሆነ በተደጋጋሚ አስገንዝቧል። አሁን ደግሞ አምባገነኑ አገዛዝ እራሱ ሊወጣ ወደማይችልበት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እየተዘፈቀ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል።የመለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ በህወሓት/ ኢህአዴግ ውስጥ የሚታየው ግልፅ ሽኩቻና ፍትጊያ እጅግ እየተፋጠነ መሄዱ ይህንኑ ሃቅ ያረጋግጣል።
ይህንን ፉክክር የሚያካሂዱት የድርጂቱ አባላት በተወሰነ ደረጃ ይቀያየሩ እንጂ፣ በመሠረታዊነት ቢያንስ ሁለት ቦታ ተፋጠው የሚገኙ ቡድኖች መከሰታቸውን መገንዘብ ይቻላል። የሸንጎን ወቅታዊ መግለጫ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ