33ቱ ፓርቲዎች ወደ “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” አደጉ

October 22, 2013

(ፍኖተ ነፃነት) 33 ፓርቲዎች እየተባሉ የሚጠሩት በ15/02/ 05 የአዳማ ፔቲሽን ተብሎ የሚጠራውን የፈረሙ ናቸው፡፡ የጋራ ስምምነት ሰነድ የፈረሙት 24 ፓርቲዎች ሲሆኑ ጥቅምት 10 ቀን በዋለው ስብሰባቸው ወደ ቅንጅት አድገዋል፡፡ እሁድ በተደረገው ስብሰባቸው የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመመስረቻ ፅሁፍና መለስተኛ የድርጊት ፕሮግራም በመፈረም “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ/ ትብብር/ በሚል ተሰይመዋል፡፡ በዚህ ውስጥ የተካተቱት 10 ፓርቲዎች ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ያልተካተቱበት ምክንያት ተብራርቷል፡፡ በተለይ መድረክ ውስጥ 6 ፓርቲዎች ቀጥታ አባል ሲሆኑ፣ ሌሎች ሶስት ፓርቲዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከመድረክ ጋር ግንኙነት ስላላቸው መካተት አላስፈለጋቸውም፡፡
በለቱ ስብሰባ አቶ አስራት ጣሴ ሰብሳቢነታቸውን ሲያስረክቡ፣አቶ ገብሩ ገብረማሪያምም ከስራ አስፈፃሚነታቸው ለቀዋል፡፡ አዲስ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የተመረጡ ሲሆን አቶ ኑሪ ሙደስር፣ አቶ አለሳ መንገሻ፣ አቶ ግርማ በቀለ፣ አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎና አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ተካተዋል፡፡
በለቱ ጎልተው ከወጡ አጀንዳዎች መካከል
1ኛ. እነዚህ ወደ ትብብር የመጡ ፓርቲዎች ወደ ቅንጅት የሚመጡበት ሁኔታ ማመቻቸት
2ኛ. ቅንጅቱ/ትብብሩ ከመድረክ ጋር የሚያሰራውን ሰነድ አዘጋጅቶ መፈረም
3ኛ. በሂደት ከመድረክ ጋር ውህደት መፈፀም የሚሉ ነበሩ፡፡
በመሆኑም እንደዋነኛ ግብ የተያዘው በ2007 ምርጫ አንድ የሆነ ግዙፍ ተቃዋሚ ለመፍጠር ነው፡፡
መረጃውን በመስጠት አቶ አስራት ጣሴ ተብብረውናል፡፡

Previous Story

ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች

Next Story

በትግራይ አንድ ቄስ ተገደሉ

Go toTop