የኖርዝ ካሮላይና መካነ ብርሃን ቅ/ሥላሴ ቤ/ክ “አዲሱን ፓትርያርክ” አባት ብለን አንቀበልም አለች

March 3, 2013

“አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤” ዮሐ ፮:፴፯

” በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው ሕገ ወጥ የስድስተኛ ፓትርያርክ ሲመት የቤተክርስቲያን የሰላም በር የሚዘጋ በመሆኑና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የመከራና የልዩነት ዘመን የሚያራዝም በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን የሚሾመውንም አባት የቤተክርስቲያን አባት ብለን የማንቀበላቸው መሆኑን ለሚመለከተው ሁሉ ለመግለጽ እንወዳለን። ከቀኖና ቤተክርስቲያን አኳያ በስደት ዓለም የሚገኙት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ር እሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ናቸው። የምንቀበለውም በቅዱስነታቸው የሚመራውን ሕጋዊውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነው” ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Previous Story

ሙስሊም ወጣቶች ከደቡብ ወሎ እየተሰደዱ ነው

Next Story

(ሰበር ዜና) የገለልተኛና የስደተኛው ሲኖዶስ አብያተ ክርስቲያናት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ” የሚለውን ስም እንዳይጠቀሙ ክስ የሚመሰርት ኮሚቴ ተቋቋመ

Go toTop