(ዘ-ሐበሻ) የአማራው ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ባህር ዳር ከተማ የሥራማቆም እና ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ተጀመረ::
በከተማዋ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ፖሊስ ብቻ ሲሆን ሕዝቡ ለቀጣይ 3 ቀናት እንዲደረግ በታቀደው ከቤት ያለመውጣትና የሥራማቆም አድማ ተሳታፊ ለመሆን በዛሬው እለት ጀምሮታል::
በባህርዳር ምንም ዓይነት ንግድ እንቅስቃሴ ካለመኖሩም በላይ ሆቴሎችን ጨምሮ ትናንሽ ምግብ ቤቶች ዝግ ናቸው::