(ዘ-ሐበሻ) ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ላይ በሰፊው እየተወራ የሚገኘው የአቶ ጁነዲን ሳዶ በወያኔ ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየገለጹ ነው። እነዚህ ለአቶ ጁነዲን ቅርብ ነን ያሉ ወገኖች “የወሬው ምንጭ ሁሌም ሕዝብን በወሬ ማራበሽ የሚወደው የወያኔ መንግስት ነው” ይላሉ።
ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሀመድ በፌስቡክ ገጹ “ጁነዲን ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት ነው” ሲል በተለይ በአያንቱ ድረገጽ ላይ የወጣውን ዜና አስተባብሏል። አያንቱ ድረ ገጽ Gurmessaa Beekamaa የተባሉ ሰው በፌስቡክ የለጠፉትን ዜና “ይህ ዜና ከነፃ ምንጮች አልተረጋገጠም” በሚል በማቅረብ ዜናው እንዲቀጣጠል ያደረገ ቢሆንም፤ ድረገጹ ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጁነዲን በሕይወት ስለመኖራቸውና ስላለመኖራቸው የተምታታ መረጃዎች እየደረሰን ነው በሚል ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝና የዜናው ምንጭ ናቸው የተባሉት ግለሰብም ስለጁነዲን ተጨባጭ ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
የወያኔ ሚዲያ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮቻናል የተባለውና በሃገር ቤት የሚታተመው ጋዜጣ ከዚህ ቀደም ጁነዲን ሳዶ ወደ ኬንያ ጠፍተዋል በሚል ሃሰተኛ ዜና ማሰራጨቱ የሚዘነጋ አይደለም ያሉት እነዚሁ የጁነዲንን ሞት የሚያስተባብሉ ወገኖች አሁንም ተገደሉ ብሎ የሚያወራው ራሱ ወያኔ፤ የሕዝቡን የአስተሳሰብ አቅጣጫ ለመቀየር ነው ይላሉ። በተለይ በነፃው ፕሬስ ላይ ለረዥም ዓመታት የሰሩ አንድ አንጋፋ ጋዜጠኛ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት “የወያኔ መንግስት ሃሰተኛ ዜናዎችን በመፈብረክ ሚዲያዎች ተአማኒነት እንዲያጡ ለማድረግ ሲጥር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በነፃ ጋዜጦች ስም የራሱን ጋዜጦች በማሳተም ሃሰተኛ ዜናዎችን እያቀረበ በራሱ ቴሌቭዥን ደግሞ ‘ነፃ ጋዜጠኛ የሚባሉት እንዲህ እያሉ የውሸት ዜና እየጻፉ ነው’ የሚል ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ራሱ በከፈተው ነፃ ጋዜጣ ሌላውን ነፃ ጋዜጣ ሲያሰደብና ተአማኒነት እንዲያጡ በማድረግ ቆይቷል። አሁን ደግሞ እንዲህ ያለው ዜና፣ ባለፈው ዓመት መንግስቱ ኃይለማርያም በዙምባብዌ ሞቱ የሚሉት ዜናዎች በራሱ በወያኔ ተዘጋጅቶ በፌስቡክ የሚለጠፈው ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንደሚያመጡ ስለሚያውቅ መንግስት ሕዝቡ ፌስቡክ ላይ የሚጻፉ መረጃዎችን እንዳያምን ለማድረግ ነው የተዘጋጀ ድራማ ነው” ይላሉ።
የጁነዲን ሳዶ ባለቤት በወያኔ መንግስት ሽብርተኛ ተብለው የታሰሩ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል። ጁነዲን የሕወሓት ተለጣፊ ከሆነው ኦሕዴድ ጋር በሚሰሩበት ወቅት በአውስትራሊያ እና በሚኒሶታ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።
ጁነዲን ሳዶ ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት ነው ተባለ
Latest from Same Tags
የሶዶ ፖሊስ ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጸመ
የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ‹‹ስቴት ፈንድ›› በሚል በየወሩ የሚሰጣቸው 340 ብር አሁን ካለው የኑሮ ሁኔታ አንጻር በቂ ባለመሆኑ እንዲጨመርላቸው ለሶዶ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ ያቀረቡ
health: ስለኮሌስትሮል ሊያውቁ የሚገባዎት 6 ነገሮች
6. ኮሌስትሮልን በጥቂቱ ኮሌስትሮል የሁሉም እንስሳት ህዋሳት አካል የሆነ የማይሟሟ ነጭ የቅባት አይነት ሲሆን በበርካታ የሰውነት ተግባራት ውስጥ ቁልፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ሆርሞን ዝግጅት ውስጥ
የወያኔ ትግሬዎች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ፤….ጦርነቶች የሚዋሹት ውሸት ሲመረመር
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) መጀመርያ በዚህ የአመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ
የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች
የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ) ======================== የመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ
ሁሉም ይናገር ሁሉም ይደመጥ!!
ከአንተነህ መርዕድ እምሩ በድሮ አጠራሩ ሻንቅላ በአሁኑ የጉሙዝ ብሄረሰብ የተማርሁት ትልቅ ነገር አለ። “በትልቆች ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገህ” እየተባልሁ በሚያሸማቅቅ ባህል አድጌ በጉሙዝ ህብረተሰብ