በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ

February 11, 2015

(ፎቶ ከፋይል)
በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ዘገበ::

እንደ ኢሳት ዘገባ ከሆነ ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል።

ማንነታቸው ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው በመሄድ፣ አቶ ተሙሻን አሸባሪዎችን አስጠግተህ ትቀልባለህ ብለው በጥይት እንደመቱዋቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሆ ብለው ሲወጡ፣ በመጡበት መኪና ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አሸባሪ የተባሉት ሃይሎች እንማን እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ነዋሪዎች ግን ምናልባትም ለምርጫ ቅስቀሳ የመጡ የተቃዋሚ አባላትን ሊሆን ይችላል ይላሉ። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

Previous Story

በዩኒቨርሲቲው ጥበቃ ከተደበደቡት ተማሪዎች መካከል የአንዱ ሕይወት አለፈ

Next Story

ተሂዶበት ከሚፈለገው ቦታ ባላደረሰ መንገድ ተመላልሶ መጓዝ ችግሩ የመንገዱ ሣይሆን የተጓዡ ነው

Latest from Same Tags

Health: ባለቤቴ እኔ የማደርገው አይጥማትም፤ ሁሌ እንጨቃጨቃለን ለምትለው ወንድ 7ቱን ከሚስት ጋር ተስማምቶ የመኖር ጥበቦችን እንካ

“ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ፤ እባካችሁ አንድ በሉኝ” ዕድሜዬ ሰላሳዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ባለቤቴም በዚሁ ክልል አጋማሽ ላይ ናት፡፡ ለአስር ዓመት ያህል በትዳር ህይወት

22 ማዞሪያ ቁጭ ብሎ ከውጭ የሚመለሱ ወገኖቹን የሚያጭደው ጉራሸትና የ6 ዲያስፖራዎች ገጠመኝ

ከዘድንግል ፈንታሁን ወደ አገራቸው ተመልሰው ለመኖር ወይም ለመስራት በሚሞክሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተዘውትሮ የሚሰማው ቅሬታ፣ በስግብግብነትና በመካካድ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። በአሁኑ ወቅት የእናት ልጅም
Go toTop

Don't Miss