በፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ አራት ደረጃዎች ዝቅ አለች

February 16, 2013

በፊፋ ወርሀዊ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ አራት ደረጃዎች ዝቅ ማለቷን የፊፋ ድረ ገጽ አስታወቀ። ብሄራዊ ቡድናችን በደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎው ያስመዘገበው ደካማ ውጤት ለደረጃው መውረድ የፊፋ ድረ ገጽ እንደምክንያትነት አቅርቧል።
በውድድሩ ላይ ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታወች በሁለቱ ተሸንፎ፣ 7 ጎል ገብቶበት አንዱን አቻ ከወጣና 1 ጎል በውድድሩ ካገባ በኋላ የየካቲት ወር ደረጃው ቀድሞ ከነበረነት 110ኛ ወደ 114ኛ አሽቆልቁሏል።
በአፍሪካ ዋንጫው ሳትጠበቅ ለፍፃሜ የደረሰችው ቡርኪናፋሶ 37 ደረጃዎችን ስታሻሽል የአፍሪካ ሻምፒዮኗ ናይጄሪያ ባለፈው ወር ከነበረችበት 52ኛ ደረጃ ወደ 30 ተቀምጣለች።
የአፍሪካን ደረጃ የሚመሩት እንደየቅደም ተከተላቸው ከአለም 12 እና 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ኮትዲቯርና ጋና መሆናቸውን ያስቀመጠው የፊፋ ሰንጠረዥ የፊፋን ወርሀዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ስፔን ፣ ጀርመንና አርጀንቲና ከፊት ሲመሩ ፥ እንግሊዝም ሁለት ደረጃዎችን አሻሽላ 4ኛ መሆን ችላለች ፣ ፈረንሳይና ብራዚል አሁንም 17ኛ እና 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ሙሉ ሰንጠረዡ ይኸው እንድወረደ፡

1 Spain 1590 0
2 Germany 1437 0
3 Argentina 1281 0
4 England 1160 2
5 Italy 1157 -1
6 Colombia 1129 -1
6 Portugal 1129 1
8 Netherlands 1108 0
9 Croatia 1059 1
10 Russia 1055 -1
11 Greece 1020 0
12 Côte d’Ivoire 999 2
12 Ecuador 999 0
14 Switzerland 993 -1
15 Mexico 968 0
16 Uruguay 950 0
17 France 929 0
18 Brazil 924 0
19 Ghana 865 7
20 Belgium 864 0
21 Sweden 863 -2
22 Denmark 825 1
23 Chile 815 7
24 Bosnia-Herzegovina 814 2
25 Mali 813 0
26 Czech Republic 797 3
27 Norway 780 -3
28 Japan 779 -7
29 Montenegro 756 2
30 Nigeria 747 22
Previous Story

የአቡነ ሳሙኤል ጉዳይ የሲኖዶሱን አባላት በትውልድ ሃገር እንዲቧደኑ እያደረገ ነው

Next Story

ጥያቄዉ የሃይማኖት ሳይሆን የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ነዉ ! አማኑኤል ዘሰላም

Go toTop