በሐዋሳ በ3 ጣቢያዎች የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም ፍርድ ቤት አልቀረቡም

June 23, 2014

(ፖሊስ ትናንት የአንድነትን ሰልፍ እንዲበተን ያደረገው እንዲህ ከተማዋን በመውረር ነበር)ከሐሙስ ሰኔ 12 ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሰኔ 14 ማታ ድረስ በከተማው በሚገኙ የተለያዩ ጣቢያዎች ከ37 በላይ የፓርቲው አባላት እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከታሰሩት አባላት መካከል አቶ በየነ መረባ የተባሉ የሐዋሳ የአንድነት ፓርቲ ፀሐፊ አንተን ፍ/ቤት አናቀርብህም ከጓደኞችህ ጋር ነው የምንቀላቅልህ በማለት ሲያስፈራሩዋቸው፣ የትኞችን ጓደኞቼን ብለው ሲጠይቁ እሱን ታየዋለህ በሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ገልጸዋል፡፡ የሰመጉ የአዋሳ ተጠሪዎች ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት እንዲያቀርቧቸው ቢጠይቁም አይቀርቡም የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

Previous Story

ማስታወቂያ – ሰላማዊ ትግል 101 መጽሐፍ በግርማ ሞገስ

Next Story

Hiber Radio: ኦብነግ በአፋርና በሶማሌ ተወላጆች መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰበው ገለጸ * የእንግሊዝ አዲስ ሕግ ጫት ያዘዋወረ 14 ዓመት ይቀጣል አለ

Go toTop