በስዊዲን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሠልፍ አካሄዱ (ፎቶዎች ይዘናል)

May 17, 2014

ከተሰማ ደሳለኝ *
*(በስደት የሚገኘው የቀድሞው ኢቦኒ መጽሔት አዘጋጅ)

ሜይ 15 በስዊዲን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ በኦሮሞ ተማሪዎች ፣በጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ላይ እየደረሰ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በማስመልከት በኢትዮጵያ ኢምባሲ በመገኘት ወያኔ እያደረገ ያለውን ጭካኔ እንዲያቆም የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞዋቸውን ገልፀዋል፡፡

ብሎገሮችና ጋዜጠኞች ይፈቱ ፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የአሸባሪዎች አይደሉም ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ተገቢ ነው ፣ንፁሃን ዜጎችን ማሰርና መግደል ይቁም ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የተፃፈለትን ብቻ ከማንበብ ያቁም፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከቁም እስር ይፈታ ….. የሚሉና ሌሎች መፈክሮችንም አሰምተዋል፡፡ በተለይ የወያኔ አምባገነንነት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር ሰላማዊ ዜጎችን ያስራል ፣ያሰቃያል ፣ የመናግርና የመጻፍ ነፃነት ይነፍጋል በተለይ የዞን 9 አባላት ምንም አይነት የአሸባሪነት ተግባር እንዳልፍፀሙ አየታወቀ ጭካኔ በተሞላበት ኢ ሰብአዊ በሆነ መንገድ ክብራችውን በሚያዋርድ መልኩ እያደረሰ ያለውን ግርፋት ባስቸኩይ እንዲያቆም ጠይቀዋል።

Previous Story

የጥርስ ህመምና መዘዙ

Next Story

ከሳዑዲ የተባረሩ ስደኞች ተመልሰው እየሄዱ ነው

Go toTop