የመድሃኔዓለም ቤ/ክ መስራች አባት አቡነ ዳንኤል ተናገሩ፤ የካህናቱ ውግዘት ሃይማኖታዊ ትርጉም የለውም አሉ

April 24, 2014

አቡነ ዳንኤልየሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ መሥራች አባት አቡነ ዳንኤል ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙት ምዕመናን ጋር ተነጋገሩ። አቡነ ዘካሪያስ አውግዣቸዋለሁ ያሏቸውን አራቱን የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ካህናትን በተመለከተም “ተናደው ያደረጉት ነገር ይሆናል እንጂ ተመካክረን የምንፈታው ነው” ብለዋል። ለሰላምና ለአንድነት የቆሙት ም እመናን እንዳስታወቁት “ብጹእ አባታችን አቡነ ዳንኤል የአቡነ ዘካሪያስን በደብረ ሰላም ሜኒያፖሊስ መድሃኒያለም የማይገባ ውግዘት የወፍ ግዝትና ምንም ሃይማኖታዊ ትርጉም የሌለው መሆኑን በድምጻቸው ገልጸውልናል። ይህንን የብጹህ አባታችን አቡነ ዳንኤል የድምጽ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።” ብሏል። ድምጹን ያዳምጡ።

Previous Story

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ የጠራውን ሰልፍ እኛ በምንለው መሠረት ካላደረጋችሁ ፎርም አትሞሉም አለ (ደብዳቤውን ይዘናል)

Next Story

የቢዚ ሲግናል፣ የጃሉድና የናቲ ማን የአዲስ አበባው ኮንሰርት ተዘረዘ

Go toTop