ህወሓት ይቅርታ እየጠየቀ ነው!

April 15, 2014

ህወሓቶች ከትግራይ አከባቢዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት የትግራይን ህዝብ ልብ ሸፍቷል፤ የህወሓት የስልጣን ዕድሜ ከአንድ ዓመት እንደማያልፍ ታውቋል። አሁን ህወሓት በምንም ምክንያት የትግራይን ህዝብ ድጋፍ ማግኘት ስለማይችል ያለው ብቸኛ አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ነው። የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት እነ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሓየ፣ ስዩም መስፍን፣ ፀጋይ በርሀና ሌሎች በህወሓት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በትግራይ ገጠር ወረዳዎች እየተዘዋወሩ በአርሶአደሩና ወጣቱ ላይ ለፈፀሙት በደል በግልፅ ቋንቋ ይቅርታ እየጠየቁ ነው። ይቅርታ መጠየቅ ጥሩ ነው። ግን ምነው ከረፈደ? በህወሓቶች የዐዞ እንባ የሚሸወድ ወጣት ካለ እስቲ እናያለን። ለማንኛውም ትዕቢተኞቹ ህወሓቶች ለይቅርታ የተዳረጉ ባሰማነው (ባጋለጥነው) ተቃውሞ ነው። በትግራይ የሚደርስ ዓፈና ላጋለጣችሁ ሁሉ ምስጋናየ ተቀበሉ

Previous Story

ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው ? (ግርማ ካሳ)

Next Story

አንቀላፍቶ የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያነቃቃው የብዙአየሁ ደምሴ “ሳላይሽ” አልበም

Go toTop