ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ(ዘ-ሐበሻ) የአቶ መለስ ዜናዊን ለጋሲ እናስፈጽማለን የሚሉት አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ወገኖች ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙን በ እስር ቤት እያሰቃዩ፤ በ ጡቷ ላይ የወጣውን እጢ እንዳትታከም ምክንያት እየፈለጉ ቢበቀሏትም ጋዜጠኛዋ ግን የዩኒስኮ ጉዋልርሞ ካኖ የአለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊ በመሆን ተሸለመች።
“ይቅርታ ጠይቀሽ እንፍታሽ” “በሰዎች ላይ መስክሪና ትፈቻለሽ” ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች እስር ላይ ባለችበት ወቅት እየደረሳት እርሷ ግን ‘ለእውነትና ለሕሊናዬ እኖራለሁ” በሚል የተፈረደባትን የ እስር ጊዜ ከመፈጸም በቀር ይቅርታ አልጠይቅም በሚለው አቋሟ የጸናቸው ጋዜጠኛና መምህርት መንግስት የሚያደርሳቸውን የተለያዩ ጫናዎች ተቋቁማ ለፕሬስ ነፃነት ላበረከተችው አስተዋጨፅኦ ይህ ሽልማት እንደተበረከተላት የጠቆመው ዩኔስኮ ለዚህ ሽልማት የታጨችውም ተቋሙ ውስጥ ባሉ ገለልተኝኛ የሚዲያ ባለሙያዎች መሆኑን አትቷል።
መንግስት ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እና ጋዜጠኞችን በግፍ ቢያስርም አለም ዓቀፍ ተቋማት ግን በግፍ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያንን ላደረጉት አስተዋጾ ሲሸልሙ እንደነበር ይታወሳል።
የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና የዘ-ሐበሻ ድረገጽ አዘጋጆች በጋዜጠኛዋ ሽልማት የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ ለመላው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ አድናቂ ወገኖቻችንና ለጋዜጠኛ ር ዕዮት ዓለሙ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን።