ኢትዮጵያዊው ላሊሳ ዲሳሳ ባሸነፈበት የቦስተኑ ማራቶን ማጠናቀቂያ ቦታ ላይ በፈንዱ ሁለት ቦምቦች ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ40 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ታወቀ።
በዚህ ውድድር ላይ ለአሸናፊነት ሲፎካከሩ የነበሩት ገብረ እግዚአብሄር ገብረማርያም እና ላሊሳ ዲሳሳን ጨምሮ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ላሊሳ ይህን ውድድር ለማሸነፍ 2:10:22 እንደፈጀበትም ታውቋል። በውድድሩም ስመጥሩው አትሌት ገ/እግዚአብሄር 3ኛ ወጥቷል።
በቦስተኑ ማራቶን ላይ ከ27 ሺህ የማያንሱ ሯጮች ተሳትፈዋል። ለዚህ ፍንዳታ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን ባይኖርም ፖሊስ ጉዳዩን እየተከታለ መሆኑን ከትንሽ ሰአታት በፊት በሰጠው መግለጫ አስታወቋል። ዛሬ ሰኞ ኤፕሪል 15 ቀን 2013 ከቀኑ 2፡45 አካባቢ ነው ሁለቱ ቦምቦች በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ የፈነዱት።
ይህን ቪድዮ ይመልከቱ፦
Medical workers aid injured people at the finish line of the 2013 Boston Marathon following an explosion in Boston, Monday, April 15, 2013. (AP Photo/Charles Krupa)
View slideshow