ለአርቲስት መሠረት መብራቴ የፍቅር ደብዳቤና ኮንትራት ታክሲ የሚልከው “አፍቃሪ” ታስሮ ተፈታ

April 7, 2013

በተለያዩ ፊልሞች ላይ በመተወን ተወዳጅነትን ያተረፈቸው አርቲስት መሰረት መብራቴን አፍቅሮ እርሷ በፈለገችበት ቦታ ሁሉ ካለ ማታከት የኮንትራት ታክሲ በመክፈልና በመላክ እንዲሁም በየጊዜው በሚያውቋት ሰዎች ሁሉ የፍቅር ደብዳቤ በመላክ የሰነበተው አፍቃሪ ታስሮ መፈታቱን ከወደ አዲስ አበባ የደረሰን መረጃ አመለከተ።

አርቲስቷ ለፖሊስ የሚያስቸግረኝ ሰው አለ በሚል ባቀረበችው ክስ የተነሳ “አፍቃሪው” ለአንድ ቀን ያህል ታስሮ መፈታቱን የጠቆሙት ዘጋቢዎቻችን በልጁ ላይ ወደ ፊት ክስ እንደሚመሰረትበት ይጠበቃል ተብሏል። አፍቃሪው የተፈታው በዋስ መሆኑንም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

አርቲስት መሠረት መብራቴ የአብይ ጾም መያዣ ዕለት አባይ የሚባለውን መኪናዋን ስታሽከረክር ከፊት ለፊቷ የነበረውን የማርሴዲስ መኪና ጋር አራት ኪሎ አካባቢ  መግጨቷን የጠቆሙት ውስጥ አዋቂዎች ማርሴዲሱ ብዙም ባይጎዳም የርሷ መኪና ግን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ጉዳት እንደደረሰበት ተናግረዋል።

በሻማ እንባ በተሰኘው ፊልም ከህዝብ ጋር የተዋወቀችው መሰረት በኋላም እንደ ‘ጉዲፈቻ’ የተሰኙ ታላላቅ ፊልሞች ላይ በመተወን በቅርቡም ለአንድ ገዳም ገቢ የሚሆን መዝሙር በመዘመር ከፍተኛ አድናቆትን አግኝታለች። አፈቀርኳት ባለው ሰው ላይ ግን ክስ መመስረቷ በሃገር ቤት አነጋጋሪ ወሬ ሆኗል እንደ ዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች።

 

 

Previous Story

ከየት ነው ያመጣት?!? (ግጥም ለአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ)

Next Story

ሰላማዊ ትግል እና የመለስ ራዕይ ዘር-የማጥራት ወንጀል ስለመሆኑ – ከግርማ ሞገስ

Go toTop