ቴዲ አፍሮ በጊዮን ሆቴል ለዳግማ ትንሣኤ ለሚያቀርበው ኮንሰርት 1.2 ሚሊዮን ብር ተከፈለው

April 1, 2014

(ዘ-ሐበሻ) የዳግማ ትንሣኤን በዓል በማስመልከት በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሙዚቃ ኮንሰርቱን የሚያቀርበው ቴዲ አፍሮ 1.2 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለው የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ።

በቅርቡ ሱዳን ካርቱም 2 የተሳኩ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን አቅርቦ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ቴዲ አፍሮ የዶን አርትና ፕሮሞሽን፣ ኤቢሲ ትሬዲንግ፣ ጄ አር የሙዚቃ ፕሮዳክሽን እና ኤ ፕላስ ኤቨንትስ የተሰኙት ድርጅቶች በጋራ ባስተባበሩት የጊዮን ሆቴሉ የሙዚቃ ኮንሰርት ለቴዲ የተከፈለው ገንዘብ ድምጻዊውን ከኢትዮጵያ ድምጻውያን ብቸኛው ተከፋይ ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።

ኤፕሪል 26 ቀን 2014 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም በሚደረገው ይኸው የጊዮን ሆቴሉ የቴዲ ኮንሰርት የመግቢያ ዋጋው ስንት እንደሚሆን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ባይኖርም በጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ ግን በከተማው በሰፊው ይወራል።

ቴዲ አፍሮ “ወደ ፍቅር ጉዞ” በሚል በጊዮን ዝግጅቱን ካቀረበ በኋላ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ሌሎች ዝግጅቶችን ለማቅረብ እንደሚንቀሳቀስ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Previous Story

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ በደሴ ከተማ ተደበደቡ

Next Story

”የሃይማኖቴን ጠላት ወርውሬ ባልገድል ሞቼ ፈጣሪዬ በደሜ ይበቀልልኝ ” ሰማዕቱ አቡነ አቡነ ጴጥሮስ (ቪድዮ)

Go toTop