ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) በሚኒሶታ የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ

March 16, 2014

(ዘ-ሐበሻ) ተበቺሳ የተሰኘውን አልበሙን በቅርቡ የለቀቀው ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) በሚኒሶታ ትናንት ማርች 15 ቀን 2014 ዓ.ም የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ።

በእናት ኢንተርቴይመንት እና በዲጄ ቢኬ አስተናጋጅነት በሚኒሶታ ራስ ላውንጅ በተደረገው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ብርሃኑን ለማየት በርካታ የሚኒሶታ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በሙዚቃውም መደሰታቸውን ከተለቀቁ ቪድዮዎች መረዳት ይቻላል። ብርሃኑ አማርኛ፣ ኦሮሚያ፣ ትግርኛና ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰብ ሙዚቃዎችን የተጫወተ ሲሆን በተለይ “አምበሳው አገሳ” የሚለውን ሙዚቃ ሲጫወት የሚኒሶታ ነዋሪ የአንድነት ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት ሲፈነጥዝ ዘ-ሐበሻ የቀረጸችው ቪድዮ ያሳያል።

አርቲስት ብርሃኑ ተዘራን ከኮንሰርቱ በኋላ ዘ-ሐበሻ አነጋግራው በሚኒሶታ የተደረገለት አቀባበል ያማረ እንደነበርና ከፍተኛ ሕዝብ በኮንሰርቱ ላይ በመገኘቱ መደሰቱን ጠቁሟል።

ከብርሃኑ ተዘራ ጋር ያደረግነውን ቃለምልልስ እስከምናቀርብ ከሙዚቃ ኮንሰርቱ ቪድዮ አንዱን እንጋብዛችሁ።

Previous Story

ኃይለማርያም ደሳለኝ እና አባዱላ ገመዳ ከ”ተንባዩ” ጋር ታዩ፤ “ቡራኬ ሰጥቻቸዋለሁ” ይላል (ፎቶ ተይዟል)

Next Story

የጠፋውን የማሌዥያ አውሮፕላን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፤ (ከዚህ በፊት 5 አውሮፕላኖች ጠፍተው እንደነበር ያውቁ ኖሯል?)

Go toTop