የግንባሩን ማኒፌስቶ ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው፤ኢትዮጵያ መስቀነኛ መንገድ ላይ ደርሳለች አለ፡፡
መድረክ ይህን ያስታወቀው መጋቢት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በግንባሩ ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ግንባሩ ዛሬ “የኢትዮጵያን ወቅታዊ፣መሰረታዊ ችግሮች መፍቻ ማኒፌስቶ” ያለውን ባለ12 ገፅ ሰነዱን ይፋ አድርጓል፡፡ ሰነዱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል የሰነዱን አስፈላጊነት የሚያብራራ መግቢያ የያዘ ሲሆን በክፍል ሁለት የሀገሪቱን ችግሮች በዝርዝር አብርርቶ የመፍትሄ ሀሳቦችን ዘርዝሯል፡፡ በመጨረሻም ባለስድስት ነጥብ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ከተላለፈው ጥሪ ውስጥም የብሔራዊ አንድነት መንግስት በጥምረት መቋቋምን የሚጠይቅ ነው፡፡
መድረክን ወክለው መግለጫውን ከሰጡት አመራሮች መሀከል አቶ ጥላሁን እንደሻው፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ይገኙበታል፡፡ ከመግለጫውም በኋላ ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ