በኢህአዴግ መተካካት በነመራ ዲንሣ

March 23, 2013
በነመራ ዲንሣ

ስምለግሰው በመተካት

ሲሿሿሙ በብልሐት
የኛ ገዢዎች የሀገር መሪ
እነ ህወሓት አሳፋሪ
ኦህዴዶችሥ አጫፋሪ
እኮ ብአዴን አቃጣሪ
ደህዴኖች አጋፋሪ።

በኢህአዴግ መተካካት

ሕዠብነበር ለመተካት የሀገርመሪ የምርጫ አባት
መሪዎቹን መርጦ በካርድ በፈቃዱ ለመተካት፣
ድምፁን ነጥቆ ገሎ አፍኖ ከለከለው
ከዚህ እድል ከቶ አራቀው አገለለው
ዜግነቱን አፍኖበት በሀገሩ ባዳ አረገው።

በኢህአዴግ መተካካት

እስከመቼ ይቀልዱ ተደላድለው እኛ እንዘን
እኮ ለምን ያፈናቅሉን እስከመቼስ ነዉ ሚገሉን
በሀገራችን ባዳ አድርገው ከእንግዲም ሊያሰቃዮን
ተመራርጠው ተተካክተዉ በአፈና ሊያኖሩን
አይሆንም በል በቃ ወገኔ
እነሳለው ኢህአዴግ ላይ አንተም ተነስ እኮ ወገኔ።

ኢህአዴግን የሚያቆመው የኔ አመፅ ያንተ አመፅ ነው
ህወሓትም የሚቀልጠው በህዝባዊ አመፅብቻነው።
ለነፃነት ሆ ነው ዛሬ ለመብታችን እንሙት ዛሬ
በኢህአዴግ መተካካት አይቀጥልም በውርደትክብሬ።
ሞት ለኢህአዴግ መተካካት!!!

 

 

 

Previous Story

የትግራይ ህዝብን ዝምታ ሲተረጎም (አብርሃ ደስታ – ከመቀሌ)

Next Story

ሰላማዊ ትግል እና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች – የማይረሳ ታሪክ በኢትዮጵያ ተሰራ! ከግርማ ሞገስ

Go toTop