ያ’ገሬና የኔ – አትክልት አሰፋ (ጋዜጠኛ) – ከቫንኩቨር

December 16, 2013

እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና፣
ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና፣
ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና፣
አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤
እናቴም ውዴ ናት፣
ሚስቴም የኔ ፍቅር፤
ልጄም ንጉሴ ነው፤
የሚጣፍጥ ከማር፤
የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣
በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤
እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው።
እኔ ግን ያገሬ፤
እኔስ የ ‘ማምዬ…
የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው።
ዲሴምበር 15/2013- ቫንኩቨር (በርናቢ)

Previous Story

(ሰበር ዜና) የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ባለበት በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወሰነ

Next Story

በሕወሓት አፈና ቢፈተንም ዓረና መድረክ በማይጨው ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

Go toTop