አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ ቀረበበት

March 19, 2013

የቀድሞው የደርግ ወታደርና በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኢሕአዴግ ደጋፊነቱ የሚታወቀው አርቲስትና የማስታወቂያ ሠራተኛ ሠራዊት ፍቅሬ አንዲትን ሴት የቲቪ ማስታወቂያ አሠራሻለሁ በሚል ለመሳሳምና ለማሻሸት ሞክሯል በሚል በአስገድዶ መድፈር ሙከራ ክስ እንደቀረበበት አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ሲዘግብ፤ አርቲስቱ ይህን ጉዳይ እንደማያውቅ ማስተባበሉንም ጋዜጣው ጨምሮ ዘገቧል።
በበማስታወቂያና በፊልም ስራ የሚታወቀው አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፤ በመድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት መወራቱን በተመለከተ ተጠይቆ “በሬ ወለደ ወሬ ነው” ሲል ማስተባበሉን የዘገበው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሠራዊት ፍቅሬ ላይ አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለፖሊስ አቤቱታ ማቅረቧን የሚናገሩ ምንጮች፣ ባለፈው ቅዳሜ “ለማስታወቂያ ስራ እፈልግሻለሁ” ብሎ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ለመሳምና ለማሻሸት ሲሞክር አመለጥኩ” የሚል ነው ብሏል ጋዜጣው በዘገባው።
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ምንጮቹ እንደሚሉት፤ የአቤቱታው ሂደት ተቋርጦ፣ ጉዳዩን በሽምግልና እንዲያልቅ መደረጉን ይናገራሉ፡፡ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፤ ሠራዊት በበኩሉ “ወሬው የበሬ ወለደ አሉባልታ ነው፤ ምንም የማውቀው ነገር የለም” ብሏል፡፡ “ካሁን በፊት ከወገቤ በላይ ብዙ ተብያለሁ፤ አሁን ደግሞ ከወገቤ በታች መጡ” በማለት ቀልድ አዘል አስተያየቱን ሠጥቷል ሲል ጋዜጣው ዘገባውን አጠናቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያሉ የማስታወቂያ ሠራተኞች እና ፊልም እና ድራማ የሚያሰሩ አርቲስቶች ለትወና የሚመርጧቸውን ሴቶች ቅድሚያ ወሲብን እንጅ መንሻ እንደሚጠይቁ፤ ይህን የማያሟሉ ሴቶች ግን ብቃቱ እያላቸውም ቢሆን ለፕሮጀክቱ ብቁ እንደማይሆኑ በተደጋጋሚ መነገሩ አይዘነጋም።

Previous Story

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም በዋስ ተፈቱ

Next Story

Hiber Radio:- የኢሕአዴግ ታጣቂዎች 17 ሰላማዊ ዜጎችን ገደሉ፤ የግድያው መንስኤው ውዝግብ አስነስቷል

Go toTop