በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በበርካታ ወንጀሎች ተጠርጥሮ የሚፈለገው ጌታቸው አሰፋን በቁጥጥር ሥር የማዋል አቅም ካለው እንዲያውል; አቅም ከሌለው ደግሞ ለሕዝብ ይህን ይፋ እንዲያደርግ ተጠየቀ::
https://www.youtube.com/watch?v=PfVYx0Ma0Rs&t=440s
የቢቢኤን ራድዮ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለዘ-ሐበሻ በሰጠው ቃል እንዳለው “ጌታቸው አስፋ በቁጥጥር ስር አልዋለም። እራሱን በራሱ አስሯል። ያለበት ሁኔታ በመንግስት ከታሰሩ ሰዎች የከፋ ነው ሲባል ብዙው ተገረመና በሰመናዊው ማእበል ተጠቃ። ግለሰቡ ትርምስ ይፈጥራል የሚል ትርክት አለ። ማእከላዊ መንግስት አቅም ካላው ለምን በቁጥጥር ስር አላዋለውም?” ሲል ጠይቋል::