የትግራይ ተወላጆች ጋምቤላን ለቀው እየወጡ ነው

January 13, 2019

ሰሞኑን በርካታ የትግራይ ተወላጆች ከጋምቤላ እየወጡ መሆኑን ፍትህ መፅሄት ዘገበ፡፡ እንደመፅሄቱ በክልሉ ይኖሩ የነበሩ ጥቂት የማይባሉ የትግራይ ተወላጆች የመኖሪያ ቤታቸውንና የንግስ ሱቆቻቸውን በመሸጥ እንዳንዶቹ በማከራየት መውጣት ጀምረዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8

የትግራይ ተወላጆች ንብረት የሆኑ ብዛት ያላቸው የባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንዲሁ በትላልቅ መኪናዎች ተጭነው ከክልሉ ሲወጡ መታየታቸውንም የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ገልጿል፡፡

በክልሉ የተከሰተ አዲስ ነገር ሳይኖር የትግራይ ተወላጆች ክልሉን ለቀው የወጡበት ምክንያት ግራ እንደገባቸው እማኙ ለመፅሄቱ አስረድተዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ብድር የተወሰደባቸው ትላልቅ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች በትገራይ ባለሀብቶች የሚመራ መሆኑንና አንዳንዶቹ ኢንቨስተሮች መሰወርም በትግራይ ተወላጆቹ ላይ ስጋት ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

Previous Story

መከላከያ በኦነግ ካምፕ ላይ የአየር ደብደባ ጀመረ | የተዘረፉት ባንኮች ሰራተኞች በኦነግ ታፍነው ተወስደዋል ተባለ

Next Story

አፋር ሰመራ ላይ ከኢትዮ ጁቡቲ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ዋለ

Go toTop