መከላከያ በኦነግ ካምፕ ላይ የአየር ደብደባ ጀመረ | የተዘረፉት ባንኮች ሰራተኞች በኦነግ ታፍነው ተወስደዋል ተባለ

January 13, 2019

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዛሬው እለት በምእራባዊ ወለጋ ቄለም አካባቢ የአየር ጥቃት መፈፀም መጀመሩ ተሰማ፡፡ አዲስ ስታንዳርድ ወታደራዊ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ጥቃቱ እየተፈፀመ ያለው በኦነግ በሚተዳደሩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ ነው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=bmsf7vBqDX8
የኦነግ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው ኦነግ ሸኔ የሚመራቸው ማሰልጠኛዎች የመከላከያው ኢላማ እንዲሆኑ መደረጉንም አስረድቷል፡፡

ይህ የማጥቃት እርምጃ የተወሰደው በትላንትናው እለት መንግታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ. የኦሮሚያ ኮርፖሬት locom ባንክ መዘረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህን ዘረፋ የፈፀሙት ታጣቂዎች ራሳቸውን የኦነግ ታጣቂ እንደሆኑ በዝርፊያው ወቅት መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በተያያዘ ታጣቂዎቹ ገንዘቡን ከመውሰዳቸውም በላይ ወደ አስር የሚሆኑ የባንኮቹን ሰራተኞች አፍነው እንደወሰዱ የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ አመልክቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ የባንኮቹ ስራ አስኪያጆች እንደሆኑና ሰዎቹ ታግተው የተወሰዱበት ቦታም እንዳልታወቀ ዘገባው ገልጿል፡፡

በትናንቱ የዜና ዝግጅታችን በምዕራብ ወለጋ ሁለት ባንኮች መዘረፋቸውን ዘግበን ተጨማሪ መረጃ እንደምናቀርብ ገልጸን ነበር:: ሆኖም በትናንትናው ዕለት ዘረፋው ቀጥሎ በዚያው በምዕራብ ወለጋ ዞን ብቻ 10 ባንኮች መዘረፋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ገመቺስ ተመስገን ተናግረዋል::

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ ከተዘረፉት ባንኮች መካከል በቀቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በመቻራ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በጋባ ሮቢ ከተማ የኦሮሚያ ህብረትስራ ባንክ ይገኙበታል። እንዲሁም በጉሊሶ ከተማ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ እና የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ፤ በኢናንጎ ከተማ ንግድ ባንክና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፤ በጫንቃ ከተማ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ተዘርፈዋል።

በሌላ ዘና ‹‹ሸኔ›› የተባለው ቡድን የያዘው ተግባር ‹‹መንግሥትን ማታለል ይመስላል›› በማለት የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ ቡድኑ መንገድ እየዘጋ፣ የከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፍ እየቀማ፣ መንገዶችን በተሽከርካሪ በመዝጋት፣ ኮት በማንጠፍ ገንዘብ በመሰብሰብ የእሱን አስተሳሰብ የማይቀበሉትን ደግሞ እያሰረና በመሬት ውስጥ እንደሚያሰቃይ ተናግረዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል::

ከተያዙበት አምልጠው አዲስ አበባ የመጡ ሰዎች ሰውነት ላይ ጠባሳና የገመድ ክርክር እንዳለባቸውም ጭምር የገለጹት ጄኔራሉ፣ የክልሉን የዞንና የወረዳ መዋቅሮችን አፍርሷል ብለዋል፡፡ የጦር መሣሪያዎች ከግምጃ ቤትና ከሚሊሻዎች በመዝረፍ ቀደም ሲል የነበረውን የሕዝብ ስሜትና ተስፋ ያጨለመ እንደሆነም አክለዋል፡፡
ይሁንና አሁን መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ከ15 ቀናት በፊት በተጀመረ ሥራ ሕግ መከላከያ እያስከበረ መሆኑን የገለጹት ጄኔራሉ ትጥቅ ማስፈታት መጀመሩን፣ መንገዶች መከፈታቸውንና የተዘጉ አካባቢዎችን ነፃ ማውጣት መቻሉን አስረድተዋል፡፡

Previous Story

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን አከባቢውን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

Next Story

የትግራይ ተወላጆች ጋምቤላን ለቀው እየወጡ ነው

Go toTop