ካሳ ተ/ብርሃንን ጨምሮ 12 አምባሳደሮች በአስቸኳይ ተጠሩ

December 17, 2018

ሸገር ታይምስ መፅሄት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን ካሳ ተ/ብርሃንን ጨምሮ 12 አምባሳደሮች በአስቸኳይ እንደተጠሩ ገለፀ፡፡ አምባሳደሮቹ ለምን በአስቸኳይ እንደተጠሩ ለማወቅ እንዳልተቻለ የጠቀሰው መረጃው የተጠሩትን አምባሳደሮች ስም ዝርዝር ታማኝ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘርዝሯል፡፡ በዚህ መሰረት የተጠሩት፡

1.አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ
2.አምባሳደር ካሳ ተ/ብርሃን
3.አምባሳደር ቶሎሳ ሻጊ
4.ፕሮፌሰር መርጊያ በቃና
5.አምባሳደር አባይ ወልዱ
6.አምባሰደር ፀጋይ በርኼ
7.አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
8.አምባሳደር ተበጀ በርኼ
9. አምባሳደር ሻሜቦ ፊጣሞ
10. አምባሳደር ሰለሞን አበበ
11.አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ
12 .አምባሳደር ኃይለሚካኤል አበራ

መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ የሚጠሩ አምባሳደሮች ሊኖሩ እንደሚችሉም ጠቁሟል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የለውጥ ሂደት ላይ እንዳለና አዳዲስ አምባሳደሮችን ወደተለያዩ አገራት እንደሚመድብ በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ ዶክተር አብይ ወደ አውሮፓ ባቀናበት ወቅት በተለይም በጀርመን በተካሄደው ዝግጅት የተለያዩ ተንኮሎችን በመስራት በስታዲየሙ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን እንዳይገኙ አስደርጓል በሚል የአውሮፓ ነዋሪዎች ይከሱታል::

ከብአዴን የተባረረውና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነው ካሳ ተ/ብርሃንም ቢሆን በቅርቡ በአንድ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የታገለ በሚል መሸለሙ ብዙዎችን እንዳስቆጣ ይታወቃል::

https://youtu.be/fabcQQpKeQU

Previous Story

አትረፍ ያለውን በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል ዘራፊዎችን ለሕግ ማቅረብ ማለት ለትግራይ ህዝብ ነፃነትና እፎይታ እንጂ ማንበርከክ አይደለም

Next Story

ባለቤት አልባ ህንጻዎች በተበራከቱባት አዲስ አበባ በመንግስት ተቋማት ያሉ ንብረቶችን ለመቆጣጠር አዲስ መስሪያ ቤት ሊቋቋም ነው

Go toTop