በነብይ እዩ ጩፋ መድረክ ላይ የታየውና አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የመከላከያ ሰራዊት አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡

November 5, 2018

በነብይ እዩ ጩፋ መድረክ ላይ የታየውና አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የመከላከያ ሰራዊት አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡

ሸገር ታይምስ መፅሄት በድረ ገፁ ዛሬ እንዳቀረበው መረጃ የመከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ባልተገባ መንገድ በተጠቀሙት ላይም ምርመራ ተጀምሯል፡፡ ከነብይ እዩ ጩፋ ጋ በተገናኘ የሰራዊቱን አልባሳት እና መለዮ በመጠቀም ያልተገባ ተግባር ፈፅመዋል በተባሉ በሰራዊቱ ውስጥ ባሉ እና በተሰናበቱ የቀድሞ አባላት ላይ ምርመራ የተጀመረ መሆኑ pንም ዘግቧል፡፡ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለቀቁት ምስሎች ላይ የታየው የመከላከያ አባልም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከዘገባው ለማወቅ ተችሏል፡፡
‹‹በምስሎቹ ላይ ከነብይ እዩ ጩፋ ጋር የታዩት አብዛኞቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከስራ የተሰናበቱ ተቀናሽ አባላቶች ናቸው›› ያሉት የሸገር ታይምስ የመረጃ ምንጮች በተደረገው ማጣራት በጭራሽ የኮማንዶ (የልዩ ኃይል) አባላት ያልሆኑ ጭምር የልዩ ኃይሉን መለዮ ለብሰው ሲንቀሳቀሱ ነበር ብለዋል፡፡
‹‹በሰራዊቱ አልባሳት የተፈፀመው ተግባር ፍፁም ወንጀል እና ተቋሙ ከተሰጠው እና አክብሮ ከሚመራበት መርህ የተቃረነ ነው›› ያሉት እነዚሁ ምንጮችን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው የሰራዊቱ መምሪያ በተሰጠ ትዕዛዝ ጉዳዩ በከፍተኛ ደረጃ እየተጣራ እና ቦታው ላይ የሚገኘው ክፍል በወረደለት ትዕዛዝ መሰረት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሆነም ነው የጠቆሙት፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=s7RE3J58cdA

Previous Story

ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ

Next Story

ሕወሓት የቅማንትን ካባ ለብሶ በመተማ ጥቃት አደረሰ

Go toTop