ክፍት ደብዳቤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሙሉ ከኦሮሞ ቄሮ የተላለፈ ጥሪ

February 23, 2018

ከሁሉም አስቀድመን ባላችሁበት ሰላምታ ይድረሳችሁ።

ሁላችንም እንደሚናውቀው የኦሮሞ ቄሮዎች ህይውታችንን መስዋዕት አዲርገን የኦሮሞ ህዝብ መብትና ብሄርቤረሰቦች እኩልነት የተረገጋጠባትን ኢትዮጽያ ለመመስረት ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ሰላማዊ ትግል ይህችን አገር እየቀየራት ይገኛል።

ይሁን እንጅ አንባገነን የሆኑ የTPLF ጥቂት ኮንትሮባንዲስቶች ቡድን አገሪቷን ለማዝረፍ በተሃድሶ መሪዎች ና በቄሮ የተዘጋባቸዉን የዝርፍያ መንገድ መልሰዉ ለመቆጣጠር ፣ አገርቷን በጦር ሀይል ለማቆጠጣር አስቻኳይ ግዜ አወጅ እያዋጁ ይገኛሉ። ይሄ አዋጅ በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት አይኖረዉም።

የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ኮንትሮባንድስቶች አገሪቷን ለመበዝበዝ እና ለመበታተን በኦሮሞ ህዝብና በመላው ብሄርቤረሰቦች ላይ የታዋጀ አዋጅ እንዲሰረዝ የበኩላችሁን የዜግነት ግደታ በመወጣት አገሪቷን ከዉድቀት እና ከመበታተን እንድታድኑ የኦሮሞ ቄሮ በዚህ ደብዳቤ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ከዚህ እልፎ አዋጁ የሚጸድቅ ከሆነ የኦሮሞ ቄሮና ህዝብ የአፀፋ ምላሽ ተጠያቂዎቹ TPLF ና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መሆናችሁን እናሳስባለን።

ከሰላምታጋር
የኦሮሞ ቄሮ”

Previous Story

ሊታይ የሚገባው ውይይት: ጀዋር መሐመድ | አሉላ ሰለሞን | አቻምየለህ ታምሩ | ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው | VOA

Next Story

ከባህር ዳር አሁን የደረሰን ቪዲዮ

Go toTop