ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የቀድሞው የሕጋዊው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረው አንዷለም አራጌ እና 746 ሌሎች እስረኞች በነገው ዕለት እንደሚለቀቁ አገዛዙ በድጋሚ አስታወቀ። ባለፈው ሳምንት እነ እስክንድር ይፈታሉ ብሎ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከገለጸ በሁዋላ ከመፈታታቸው በፊት የግንቦት 7 አባል ነኝ ብላችሁ ፈርሙ የሚለውን ቅድመ ሁኔታ በመቃወም ዛሬም ድረስ አለመፈታታቸው ይታወቃል።
በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አገዛዙ ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክረዋል በሚል የፈጠራ ወንጀል አስሮ ያስቀመጣቸውና ባለፈው ሳምንት እነ እስክነንድር ይፈታሉ ሲል ስማቸውን አልጠቀሳቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ዘጠን የፖለቲካ እስረኞች ቄሮ በጠራው የሶስት ቀን ስራ ማቆም አድማ በሁለት ቀኑ የተሳካ አድማ ግራ የተጋባው አገዛዝ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ዛሬ መፍታቱ ይታወሳል።
አቶ በቀለ ገርባ ፣አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጌቱ ጋሩማ፣ አቶ ተስፋዬ ሊበን እና አቶ በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጦ ዛሬ ከተለቀቁ በሁዋላ በአዳማና ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ማምሻውን አደባባይ ወጥቶ በስታውን እየገለጸ ተቀብሏቸዋል። ተፈተዋል ከተባሉት አቶ አዲሱ ቡላላ ሳይፈቱ መቅረታቸው ታውቋል።በእስረኞቹ መፈታት ቄሮ ከአዳማ ውጭም በተለያዩ ቦታዎች ደስታውን እየገለጸ ይገኛል።
ቄሮ ለሶስት ቀን የጠራው አድማ አብይ ጥያቄ ሁሉም የህሊናና ፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣በግፍ እየተፈጸመ አለው ግድያ እንዲቆም ሲሆን የእነ አቶ በቀለ ገርባን ያለ ቅድመ ሁኔታ መፈታት ተከትሎ የነገው አድማ መቋረጡን አስቀድሞ ማሳወቁን ዘግበናል። በነገው ዕለት ቄሮ ለተቃውሞው የዘጋውን መንገድ እንደሚያጸዳ የገለጸ ሲሆን የሐማሬሳውን የሕሁድ ከሶማሌ ክልል በተፈናቀሉና ሜዳ ላይ በመጠለያ ስም በሚኖሮ ተፈናቃዮች ላይ የተወሰደው ጭፍጨፋ ተቃውሞው አጠናክሮታል።