(ዘ-ሐበሻ) የ8 ልጆች አባት የሆኑት ሼህ መሀመድ አላሙዲ ፎርብስ የተባለው መጽሔት በየዓመቱ ከሚያወጣው የሃበታሞች ደረጃ ከ2013 የዓለማችን ትላልቅ ቢሊየነሮች መካከል 65ኛው መሆናቸውን አስታወቀ። ከሳዑዲ አረቢያዊ አባታቸው እና ከኢትዮጵያዊ እናታቸው የተወለዱት አላሙዲ ገንዘባቸውን ኢንቨስት ማድረግ የጀምሩት በ1970ዎቹ እንደሆነ ያስታወቀው ፎርብስ ኒውስ በኢትዮጵያም ትላልቅ ገቢ በሚያስገኙት የወርቅ፣ የሲሚንቶ፣ የእርሻና የሆቴል ሥራዎች ላይ እንደተሰማሩ መጽሔቱ ገልጿል።
የ68 ዓመቱ ዕድሜ ባለሃብት አላሙዲ የ2013 የፎርብስ የዓለማችን 65ኛው ሃብታም ሲሆኑ በአንደኝነት የተቀመጡት ሜክሲኳዊው ካርሎስ ስሊም እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው። 73 ቢሊዮን ዶላር አላቸው።
2ኛ. ቢልጌትስ 67 ቢሊዮን ዶላር
3ኛ. አማናኮ ኦርቴጋ 57 ቢሊዮን ዶላር
4ኛ. ዋረን ብፌት 53 .5 ቢሊዮን ዶላር እንዳላቸው ፎርብስ ገልጿል።
በየዓመቱ ማርች ላይ የሃብታሞችን ዝርዝር የሚያወጣው ፎርብስ አላሙዲ ከዓለም 65ኛው ሃብታም ሲሆኑ ይህም በሳዑዲ አረብያ 2ኛው ሃብታም ያደርጋቸዋል። ያላቸውም ሃብት 13.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ መጽሔቱ አስፍሯል። አላሙዲ በ2012 ዓ.ም የነበራቸው ሃብት 12.5 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ዘንድሮ ዕድገት ማሳየቱ የፎርብስ የሁለት ዓመቱ ሪፖርትን በማየት ማወቅ ይቻላል። ሆንም ግን አምና አላሙዲ ከዓለም ሃብታሞች 61ኛው የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ 4 ደረጃ ዝቅ ብለው 65ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።