ማሳሰቢያ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ሕብረት
ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ እና ለቦንጋ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ በሙሉ ፦ ሠሞኑን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች መረዳት እንደተቻለው በቅርቡ የመማር ማስተማር ሥራውን የጀመረው የቦንጋ ዩንቨርስቲ ውስጥ በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ያስነሱዋቸው የመብት ጥያቄዎችን ተከትሎ አመፅና ብጥብጥ መፈጠሩ ይታወሳል።
በመሆኑም የመብት ጥያቄውን ተከትሎ የተነሳውን ብጥብጥ የኦሮሞ ተማሪዎች ብቻ ሆን ብለው አመፅ ለመፍጠር ተነሳስተው እንዳደረጉት በመቁጠር የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በወያኔ ካድሬወችና በተለያዩ ደጋፊ አካላት እየተነዛ ይገኛል።
ወያኔ አሁንም ራሱን አዋቅና ብልጥ አደርጎ እየቆጠረ ያለ ይመስለዋል። በጣም የወረደና የዘቀጠ አስተሳሰብ ይዞ ብሄርን ከብሄር ሊያጋጭ ይፈልጋል። የምገርመው የካፋ ሕዝብ ወይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ የቦንጋ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ እንደዚህ ዓይነት ተራና መሰረተብስ የወያኔ ካድሬዎችን ወሬ የምሰማበት ጊዜ ላይ አይደሉም። እንደዚህ ዓይነቱ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የተከበረውን የኦሮሞንና የካፋን ህዝብ ለማጋጨት እና ተማሪዎች መብታቸውን ለማስከበር የሚያደርጉትን ትግል ለማኮላሸትና ለማቀጨጭ ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ መሆኑን ሁሉም ሊረዳው ይገባል። የካፋና የኦሮሞ ሕዝብ ድሮ የነበረ፥ አሁን አብሮ የሚኖርና ለወደፊትም አብሮ የሚኖር ሕዝብ ነው። ይልቁንም የትግሉ አካል መሆን እየተቻለ ችግሩን የአንድ ወገን ብቻ ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑን መላው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና የቦንጋ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ በጥልቀት በመገንዘብ እንደዚህ ዓይነቱንና ተዛማጅ የመብት ጥያቄዎች ከሚያነሱ ታጋዮች ጎን እንዲሠለፍ በተለይም ከቄሮና ከፋኖ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዦ ይህንን መንግሥት ነኝ ባይ ዘራፊን እንድናስወግድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።