(ዘ-ሐበሻ) ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በቺካጎ ከተማ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 28 ቀን 2013 ሕዝባዊ የውይይትና የምክክር ስብሰባ መጥራቱን አስተባበሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ በላኩት በራሪ ወረቀት አስታወቁ።
በተጠቀሰው ዕለት ከ12:30 ፒኤም ጀምሮ በLoyola Park recreation Center (1230 W Greenleaf Ave., Chicago, IL 60626) ይደረጋል በተባለው በዚሁ ሕዝባዊ የውይይትና የምክክር ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው እንደሚገኙና ሕዝቡን እንደሚያወያዩት ተገልጿል። የቺካጎውን ስብሰባ ያስተባበሩት ወገኖች ለዘ-ሐበሻ የላኩት በራሪ ወረቀት (ፍላየር) የሚከተለው ነው፦