እኔ ያልኩት እየተሰራበት ያለውም
1) የኦሮሞ ሲቪክ እና ፖሊቲቻል አመራር በቅርቡ በመሰብሰብ የኦሮሞ ቻርተር ያዘጋጃል። ይህ ሁሉንም ዮሮሞ አመራሮች ሊሳማማ የሚችል አነስተኛ ፕሮግራም ማለት ነው
2) ወያኔ እየወደቀ ስለሆነ ከዚያስ ምን መሆነ አለበት በሚለው የፖሊሲ የስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ኮንፈረንሰ በቅርቡ በኦሮሞ የህግ ባለሟያዎች ማህበር ሎንዶን ላይ ተጠርቷል
(( ለመላው ኢትዮጲያም እንዲህ አይነት Social Contact ያስፈልጋል፤ እያንዳንዱ ማህበርሰብ መጀመሪያ በውስጡ እንዲህ አይነት ስምምነት ፈጥሮ ቢቀርብ ይሻላል በማለት ባለፈው ኢትዮትዩብ ባዘጋጀው ፎረም ላይ መናገሬ ይታወስ)
https://www.youtube.com/watch?v=oFQ7IZRBjx0
3) የኦሮሞን ህዝብ መብት እና ጥቅም በዘላቂነት ለማስከበር ከፖሊቲካ ፓርቲዎች ወገንተኘት ነጸ የሆነ ወታደራዊ ተቋም መቋቋም አለበት
ይህ አዲስ ንግግር ሳይሆን ላለፉት ብዙ ወራት እና አመታት በኦሮምኛ፣ አማርኛ እና እንጊሊዚኛ ያቀርብኩት ንግግር ነበር። ይህን ስናገርም የንግግሩን ጭብጥ ደጋግሞ ለሰማ ማህበረሰብ ስላነበር ዝርዝር ውስጥ አልገባሁም። ዋዜማ ወይ የትርጉም ችግር ነበረበት ወይም ከኮንቴክስቱ ውጪ ነው የተረዳው መሰለኝ።