ከወልቃይት ዐማራ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የታሰረው ዐማራ በቂሊንጦ ተገደለ

September 15, 2016

ሙሉቀን ተስፋው
ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ በመግደል፣ በማሰርና በማሰደድ ጥያቄውን ለማፈን እየሞከረ ባለበት በአሁኑ ሰአት ከማንነት ጥያቄው ጋር በተያያዘ በቂሊንጦ ታስረው የነበሩ አቶ ይላቅ አቸነፍን ገድሎ ዛሬ አስከሬኑን አስረክቧል፡፡ አቶ ይላቅ አቸነፍ በላይ አርማጭሆ የትክል ድንጋይ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄን ይደግፋሉ ተብለው ከታሠሩ ሰዎች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡
የቂሊንጦን ማረሚያ ቤት በጥይት ገድሎና በእሳት ጠብሶ ካሰነበተ በኋላ ዛሬ አስከሬናቸውን አስረክቧል፡፡ የአቶ ይላቅ አቸነፍ ቀበር ሥነ ሥርዓት ከጎንደርና ከአርማጭሆ በተሰበሰቡ ዐማሮች በአሁኑ ሰአት (መስከረም 5 ቀን 2009 ዓ.ም.) እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ወያኔ የኮሚቴ አባላቱን እያሳደደና እያገደለ የማንነት ጥያቄውን ማፈን እንደ ስትራቴጂ አሁንም ድረስ እየተከተለው ያለ ቢሆንም የዐማራ ሕዝብ ትግል ግን ያሸነፋል፡፡ ያለጥርጥር ትግላችን በተሰው ጀግኖቻችን ደም ወደ ፊት ይገሰግሳል፡፡

Previous Story

1 የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞና የህዝባዊ አመፅ እንድምታዎች (ያሲን መ. ያሲን)

Next Story

Video: ኢትዮጵያን ዛሬም ያለቅሳሉ

Go toTop