(ዘ-ሐበሻ) ወደ አዋሳ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ ከፍተኛ የሰው ሕይወት አለፈ።
ደደቢት የስፖርት ክለብ ሻምፒዮን መሆኑ በታወቀበት በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአዋሳ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስን ተስተካካይ ጨዋታን ለመከታተል ወደ አዋሳ ሲጉዙ በነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ 2 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ተጨማሪ ሰዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የ2012 ሪፖርት መሰረት በዓለማችን በዓመት 1ሚሊየን 3 መቶ ሺ ህዝብ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ሲታወቅ በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ደግሞ በዓመት ክ2000 ሰዎች በላይ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያልፋል።
ለመኪና አደጋ መንስኤ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል በፍጥነት ማሽከርከር፣ ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ የሌሊት ጉዞ፣ ደርቦ ማለፍ፣ ከአቅም በላይ መጫን፣ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና ጠጥቶ ማሽከርከር ከመንስኤዎቹን መሀል ዋነኞቹ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ብልሽት፣ የእግረኛ ግራ መንገድ ይዞ አለመሄድና የማቋረጫ ምልክቶችን (ዜብራ) በአግባቡ አለመጠቀም፣ የመንገዶች በጥራት አለመሰራትና የመንገድ ላይ ምልክቶች ተሟልተው አለመዘጋጀት ለአደጋው እንደመንስኤ የቀረቡ ናቸው፡፡ ትናንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላይ የደረሰው የመኪና አደጋ መንስኤ እየተጣራ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች ዘ-ሐበሻ እንደደረሷት ታቀብልዎታለች።