የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን ለዘንድሮው 30ኛ ዓመት ውድድር አሸኛኘት ተደረገልት
የፌዴሬሽኑ ቦርድ ተጫዋቾቹ እንዲመጡ ቢወስንም ፕሬዝዳንቱ ውሳኔው ውድቅ ሆኗል ሲሉ ማስፈራሪያ ሰጥተዋል
ቅዳሜ በሚደረገው የቦርድ ስብሰባ የመጨረሻ ምልሽ ይጠበቃል
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቦድን አባላት ዘንድሮ ዲሲ ላይ ለሚደረገው ጨዋታ ለመሳተፍ ከሄዳቸው በፊት ትላንት በከተማው በኮሚኒቲው አባላት በአንድ የሕዝብ መናፈሻ ውስጥ በተካሄደ ስነ ስርዓት አሸኛኘት ተደረገላቸው።
የቡድኑ አባላት ከዓመት በላይ ለፌዴሬሽኑ የቀድሞው የቡድኑበፌዴሬሽኑ ተወካይ በነጻ ምርጫ ስልጣኔን አለቅም በማለቱ ውክልናውን አንሱ አታንሱ ቡድኑ የሕዝብ እንጂ የግለሰብ አይደለም የሚል ተቃውሞ ያቀረቡ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ቦርድ ለማስማማት የተለያዩ ጥረቶች ቢያደርግም ግለሰቡ የቦርዱን የማስማሚያ ሀሳብ ባለመቀበሉ ቦርዱ በአብላጫ (ሞሽን ) ተጫዋቾቹ ለዘንድሮው ውድድር እንዲገኙ ቢወስንም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን ተጫዋቾቹም አይወክለንም ባሉት ወኪል ስር ካልሆኑ በቀር በመጪው ቅዳሜ ያልጠበቁት እንደሚጠብቃቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ መግለጻቸውን ተጫዋቾቹ ለህብር ሬዲዪ ገልጸዋል።
ህብር ሬዲዮ የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንት ስለ ሰጡት ቃለ መጠይቅ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ቢሞክርም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አያነሱም።ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ሙከራ አድርገናል።
በትላንቱ የቬጋሱ የኢትዮ ስታር ቡድን አባላት የሽኝት ፐሮግራም ላይ የቬጋስ የኢትዮጵያ ኪሚኒቲ የወቅቱና የቀድሞ አመራሮች መካከል ጥቂቶቹ ፣ በቡድኑ አባላት መካከልና ከስልጣን አልወርድም ባለው ግለሰብ መካከል በከተማው ከዚህ ቀደም ሽምግልና በማድረግ ግለሰቡ ምርጫ አይደረግም በማለቱ አባላቱ ምርጫ እንዲያደርጉ የወሰነው የሽማግሌዎች ቡድን አባላት፣ የቀድሞ የቡድኑ እኛ የሰሜን አሜሪካ የኢጥዮጵአውያን ስፖርት ፌዴሬሽን መስራች አንዱ አቶ ዘውዱ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች በስፍራው ተገኝተው አሸኛኘት አድርገዋል።የቡድኑ አባላት ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁት ቶምቦላ ዕጣም ወጥቷል።
በቬጋስ የኢትዮጵያ ኮሞኒቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ሽመልስ የፌሬሽኑ በቡድኑ አባላትና በተወካዩ መካከል የነበረውን ችግር ከዓመት በላይ ሳይፈታ በአሁኑ ወቅት ከከተማው መሰለፍ የሚገባው አንድ ቡድን ሆኖ ሳለ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ግለሰቡም የራሱን ቡድን ይዞ ሁለት ቡድን እንዲኖር መደረጉ ያሳዝናል ብለዋል።
<<ይሄ የሕዝብ ቡድን ነው። ለዕውነት መብታችሁን ለማስከበር ባልመረጥነው ሰው አንተዳደርም ቡድኑ የሕዝብ እንጂ የግለሰብ አይደለም በማለታችሁ የፌዴሬሽኑ አመራር በተለይ ፕሬዝዳንቱ ከግለሰቡ ወግኖ እስከዛሬ መግፋቱና አሁንም ማስፈራራቱ ያሳዝናል።ይሄ ቡድን የቬጋስ ወኪል ነው >> ያሉትአቶ ገዛኘኝ ተፈራ ባለፈው ዓመት በቡድኑ አባላት እና ከስልጣን አልወርድም ባለው የቀድሞ የቡድኑ ዋና ጸሐፊ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትበኮሚኒቲው የተቋቋመው የሽማግሌዎች ቡድን ሊቀመንበር ሲሆኑ <<መልካም እድል ይግጠማችሁ >> ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡንድ ችግር የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ትልቅ ራስ ምታት መሆኑንና ከዚህ ቀደም የቡድኑ አባላትና ተወካዩን ለማስማማት ትልቅ ጥረት ቢደረግም አለመሳካቱን የፌዴሬሽኑ የውድድር ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተካበ ዘውዴ ባለፈው ዕሁድ ለህብር ሬዲዮ የገለጹ ሲሆን ተአምር መጠበቅ ቢሆንም በቅዳሜው ወሳኝ የፌዴሬሽኑ የቦርድ ስብሰባ ላይ ከየአቅጣጫው ችግሩን በሽማግሌ ለመፍታት የሚያስቡ ስላሉ ውጤት ይገኝ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳለው ገልጿል።
የፌዴሬሽኑ ፕ/ት አቶ ጌታቸው በበኩላቸው ለአንድ ሬዲዮ ባለፈው ዕሁድ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የቡድኑ አባላት አልመረጥነውም አይወክለንም ያሉትንና በስልታን ለመቆየት ድምጽ ለማግኘት ሲሉ ይደግፉታል፣ድምጻችንን አፍነዋል የሚለውን ወቀሳ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ተጫዋቾቹ አይወክለንም ያሉትንና ለጊዜው በተወካይነት ዘንድሮ ከቡድኑ ጋር ሆኖ ተጫዋቾቹ በውድድሩ ይሳተፉ የሚለውን የቦርዱን የአብላጫ ውሳኔ ውድቅ መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ጠቅመው በመጪው ቅዳሜ ተጫዋቾቹ ያልጠበቁት ይጠብቃቸዋል ሲሉ አስፈራርተዋል።
<<እንዴት ኢትዮጵያውያንን በሚያገኛኘው መድረግ ላይ ያለ አንድ የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ያልወከልነውንንና የስልጣን ጊዜው ገደብ ይኑረው ቡድኑ የግለሰብ ሳይሆን እያንዳንዱ ተጫዋች ተሰሚነት ያለው የከተማው ቡድን ነው ባልን ያስፈራሩናል? ያሳዝናል>> ሲል የፕሬዝዳንቱን አስተያየት መሰረት አድርጎ አንድ የቡድኑ አባል ለህብር ሬዲዮ ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴሬሽኑ ነባር አባልና ከመስራቾቹ አንዱና የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ቡድን መስራች አቶ ዘውዱ ታከለ ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በግልባጭ ለቦርድ አባላት የሚደርስ የቅሬታ ደብዳቤ ጻፈ።በዚህ በደብዳቤው ፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው በጻፈው ደብዳቤ ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች እንጂ በቦርድ አባላት አለመመስረቱን፣ በተለይ ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ተጫዋች አንቀበልም ብሎ በድምጹ ይውረድ ያለውን ግለሰብ በመቀበል የተጫዋቾችን ድምጽ ውድቅ ማድረጋቸውን ወቅሷል።የቬጋሱን ኢትዮ ስታር ቡድን ግለሰቡ ስም ቀይሬ እንደ ግል ንብረቱ በሱ ፈቃድ ማስመዝገቡን ጠቅሷል።ፕሬዝዳንቱ ከተጫዋቾቹ እውቅና ውጭ ግለሰቡን የሳቸው ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ከህግ አግባብ ውጭ ይደግፉታል ብሏል።
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር ክለብ የቀድሞ የቡድን ተወካይና ዛሬም በፌዴሬሽኑ በቦርድ አባልነት የሚገኘው አቶ ሙላት መለሰ በቅርቡ የፌዴሬሽኑ ቦርድ ጊዜያዊ የማስማሚያ ሀሳብ አቅርቦ እሱና ከቡድኑ አባላት መካከል አቶ ሲራክ ተወክሎ ቡድኑ በዘንድሮው ውድድር ተሳትፎ ቦርዱ በቀጣይ በሚያደርገው ውይይት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ይሰጣል ቢልም ግለሰቡ አልቀበልም በማለቱ ቦርዱ ወደ ድምጽ መሄዱን አቶ ጥላሁን ፍስሐ የሳንዲያጎ ቴዎድሮስ ቡድን ተወካይና የቦርዱ አባል ለህብር ሬዲዮ ገልጸዋል።
አቶ ሙላት በሳቸው ተወካይነትና በሳቸው ቡድን መጫዋት የፈለገ መጥቶ ችሎታው ተገምግሞ መሳተፍ ይችላል በማለት የቡድኑ አባላት ማንንም አትጫወት አላልንም በራችን ክፍት ነው ብለዋል። ባለፈው ዓመት ከዳላስ ውድድር በፊት አቶ ሙላት ስልጣኔን አስረክባለሁ ቢሉም በከተማው በተያዘ ሽምግልና ስልጣንዎን ለማስረከብ ማረጋገጫ ይፈርሙ መባላቸውን ተቃውመው የራሳቸውን አዲስ ቡድን መስርተው ፌዼሬሽኑም ተቀብሎ ለዓመታት በቡድኒ ውስጥ የተጫወቱ ተጫዋቾች ድምጽ ሳይሰማ ቀርቷል። በዳላሱ ውድድር እንሳተፋለን ብላችሁ ከመጣችሁ በፖሊስ እናስወጣችሁዋለን ለችግሩ መፍትሄ የምንሰጠው በኦክቶበር በምናደርገው ውድድር ነው መባላቸውን የሚገልጹት ተጫዋቾች በወቅቱ ፌዴሬሽኔ ችግር ላይ ስለሆነ ዳላስ ሳይሄዴ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ሲጠብቁ ቢቆዩም ዛሬም ድረስ ውሳኔ አላገኘም። አቶ ሙላት ዘንድሮም በግላቸው ባዝመዘገቡት ኢትዮ ስታር ፋሲለደስ በሚል ፈቃድ የራሳቸውን ቡድን አባላት አሰባስበው ለመሳተፍ የሚሄዱ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ከቦርዱ ተለይተው የምንቀበለው ሙላትን ነው በማለት ዘንድሮም ተጫዎቾቹ እንዳይሳተፉ ማስፈራራታቸውን የቡድኑ አባላት በቅሬታ ገልጸዋል።
<<በኣለፈው ዓመትም ዓላማቸው ስንከለከል ተለጣፊው ፌዴሬሽን እንድንሄድና ይሄው ወያኔዎች ናቸው ለማለት ነበር።አሁንም ዲሲ ቦርዱ ይምጡ ሲል ፕሬዝዳንቱ የሚገፉን እሳቸው የሚደግፉትን ያልመረጥነውን ተወካይ ካልተቀበልን ተገፍተን የት እንድንሄድ ነው? ከእናት ፌዴሬሽናችን የትም አንሄድም።ቦርዱ የፌዴሬሽኑ በህግ የበላይ ባለስልጣን ነው ህግ ይከበር ሲሉ በትላንቱ የቬጋሱ ክለብ ዝግጅት ላይ ያነጋገርናቸው አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።
<<ከዚህ ሁሉ ችግር ፌዴሬሽኑ ለምን በቬጋስ ሁለት ቡድን እንዲኖር አይፈቅድም? >> በሚል አቶ ተካበ ዘውዴን ቀደም ሲል ጠይቀናቸው <<የፌዴሬሽኑ ሕግ አይፈቅድም። በተወሰነ ቀን የሰላሳ ቡድን ውድድር ማድረግ በራሱ ከባድ ነው።ጠዋት የጀመርን በየቀኑ ማታ ነው የምንጨርሰው።እድል ላላገኙ ከተሞችም እድል መሰጠት አለበት>> ሲሉ ለህብር ሬዲዮ ገልጸዋል።
በ30ኛው ዓመት የፌዼሬሽኑ ዓመታዊ ውድድር ላይ ቦርዱ እንዳለው ተጫዋቾቹ ይሳተፋሉ ወይስ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሚቀበሉት የቡድኑን ተወካይ ብቻ ነው? ቀጣዩ ቅዳሜ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳዩ እልባት ያገኝለታል ብለው የሚጠብቁ አሉ ። ተከታትለን እንዘግባለን።