ለክህደቱም በሰሜን አሜርካ የሚኖሩ ግብረ አባሮቹ ፓስተሮች እና የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች በድርጊቱ ዋና ተዋናዮች ናቸው::
“ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።” ምሳ 12: 22
ቢንያም መንገሻ September 25,2015
ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ከዚህ ቀደም የሰው ህጋዊ ሚስት በዝሙት እርኩሰት በማስነወር ለቀረበበት አቤቱታ ከረጅም ማንገራገር ቡኋላ በሚያደራድሩት የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች እና እርሱን ለፓስተርነት በቀቡት የቤተክርስትያን መሪዎች ፓስተር ወዳጆቹ አማካኝነት አስነዋሪ ድርጊቱን ማድረጉን በግልጽ አምኖ ተቀብሎ ይቅርታ መጠየቁ በሁላችንም ዘንድ የሚታወስ የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው:: እንደ ኢትዮጵያን አቆጣጠር በመስከረም ወር በወሩ መጀመሪያ ቀን 2008 ዓም አካባቢ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት መቀመጫነቱ በሰሜን አሜርካ ላደረገው ዘ-አበሻ በሚባል የሚታወቀው የዜና አውታር ላይ የክህደት መልስ የመለሰው ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ለሶስተኛ ግዜ የአምላኩን ስም ተጠቅሞ ሰው ያደረገውን ኋያሉ እግዚያብሔርን ሽምጥጥ አድርጎ ክዶታል:: ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ዘ-አበሻ በሚባል የሚታወቀው የዜና አውታር እንዲህ ነበር ያለው:: “ሆቴል ክፍል ውስጥ ገብታ በጣም ስትፈታተነኝ ሌላ ጊዜ ፍላጎትሽን አሟላልሻለሁ አልኳት እጂ አልነካኋትም” “ቤተክርስቲያን መጥተው ያሰቡትን ያህል እኔን የጎዱኝ እና ያዋረዱኝ ስላልመሰላችው ቪ ኦ ኤ ሄደው ፓስተር ተከስተ አስገድዶ ደፍሮኛል ጉዳዩም በህግ ተይዞአል የሚል በሽምግልናው ወቅት በጭራሽ ያልተነሳ ሌላ ተጨማሪ የውሸት ታሪክ ፈጠሩ። ይህን አላማ እንዲያስፈጽም ጋዜጠኛ አዲሱ አበበን ይዘው መጡ። አቶ አዲሱ ጋር ስንነጋገር ሆን ብሎ እኔን ለማጥቃት እንዳሰበና እውነቱን ማወቅ እንደማይፈልግ ስለገመትኩ በጉዳዪ ለይ ምንም አይነት ኢንተርቪው ላንተ አልሰጥም፣ ጉዳዪም በቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ተይዟል አልኩት። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ጉዳዩን የያዙትም ሽማግሌዎችም አቶ አዲሱን ይሄ የቤተክርሰቲያን ነገር ነው በዚህ ነገር ላይ ምንም አይነት ፕሮግራም በሬዲዩ ላይ መሥራት የለብህም ብለው እየነገሩትና እየተለመነ በማን አለብኝነት ጉዳዩን አጣሞ ሁላችሁም እንደሰማችሁት እኔን በሚያዋርድ ፣ስሜን በሚያጠፋ፣ ሕይወቴንና አገልግሎቴን በሚያበላሽ መልኩ ፕሮግራሙን ሰርቶ በሬድዮ አቀረበው።”
የእግዚያብሔር ቃል ስለሚክዱ ውሸታም ሰዎች ዋና አፈጣጠራቸውን ምንጩ ማን እንደሆነ እንዲህ ይናገራል:: “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8:44
ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት የአምላኩን ስም ተጠቅሞ ሰው ያደረገውን ኋያሉ እግዚያብሔርን ለሶስተኛ ግዜ ሽምጥጥ አድርጎ ለምን ካደ?
ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ግልጽ ክህደትን ሁላችንም የሚያስታውሰን እና የምናውቀው አንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ ትልቅ ታሪክ አለ:: ይህም ታሪክ የእግዚያብሔር ሐዋርያው የቅዱስ (ስምኦን) ጴጥሮስ የክህደት ታሪክን እናገኛለን:: ሐዋርያው (ስምኦን) ቅዱስ ጴጥሮስ በአስጨናቂው ሰአት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሶስት ግዜ የካደው በዘመኑ አይሁድ ለአምላካቸው ካላቸው ታላቅ ቅናት የተነሳ ለመበቀል በድንጋይ ወግሮ የመግደል የሀይማኖታዊ ልማድ ነበራቸው:: ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ (ስምኦን) ጴጥሮስም በድንጋይ ተወግሮ ሞትን ፍራቻ ብቻ ጌታውን ኢየሱስ ክርስቶስን ሶስት ግዜ መካዱ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታ ኢየሱስ ላይ የተናገረው የክህደት ቃል እራሱን ክፉኛ የተጸጸተበት እንዲሁም እራሱን የወቀሰበት ምርር ብሎ ያለቀሰበት ድርጊት እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በግልጽ ተጽፎ እናገኘዋለን:: ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የጠራው እራሱ እግዚያብሔር ስለነበር እስከመጨረሻ የህይወት ዘመኑ ህይወቱን ለእግዚያብሔር ወንጌል አሳልፎ እንደሰጠ እና እንደተሰዋ መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ያስተምረናል::
ወደ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ክህደት ስንመለስ ዘንዳ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት እግዚያብሔርን ሶስት ግዜ የካደው በድንጋይ ተወግሮ እንዳይገደል:: ወይንም በሴፍ እራሱን ተቀልቶ እንዳይገደል ሳይሆን የአምላኩ የእግዚያብሔርን ስም ጠርቶ ዘፍኖ የሚኖርበትን መተዳደሪያ ስሙ እንዳይጠፋበት በማሰብ ብቻ ነው:: “ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2ጴጥ2:1-3
ከእራሱ ከእግዚያብሔር ዘንድ ተመርጠው በዝሙት ወጥመድ ተይዘው የወደቁ ታላላቅ የእግዚያብሔር ሰዎች ስማቸው እና ምግባራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተጽፎ እናነባለን:: ከእነዚህም መካከል የእሰይ ልጅ ንጉስ ዳዊት፣ የንጉስ ዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰለሞን እና ጸጉራሙ እና ሀያላኑ ሳምሶንን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል:: እነዚህ የእግዚያብሔር ሰዎች በእግዚያብሔር ላይ እጅግ ክፉ የሆነውን ሀጥያት በሰሩ ግዜ አልሰራንም አላደረግንም ብለው አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ሽምጥጥ አድርገው አልካዱም:: እንዲያውም ማቅ ለብሰው ባደባባይ ወዮ! አምላካችን እግዚያብሔርን በድለናል ብለው የንስሀ ጬኀት በመጮህ እግዚያብሔርን ይቅርታ ጠየቁ እንጂ በየትኛውም ቦታ ሲያስተባብሉ እና ሲክዱ አልታዩም:: ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ግን ከእግዚያብሔር ስላልተጠራ ሀጢያት በሰራ ግዜ በዙሪያው ምስክሮቹን አስቀምጦ ለሶስተኛ ግዜ ካደ እንጂ በድርጊቱ ተጸጽቶ ንስሀ አልገባም:: ይህ የሚያሳየን ነገር ደግሞ ሀጢያት እርኩሰት ሲያደርጉ ሳይዋሹ እና ሳይክዱ መጸጸት እና ንስሀ መግባት የሚችሉት አገልጋዮች ከእግዚያብሔር ዘንድ የተጠሩ ብቻ መሆናቸውን ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ህይወት አስረግጦ ያስተምረናል:: “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።” 1 ዮሐ 1:8_10 “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ምሳ 6:16_19