ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ረቡዕ መስከረም ፲፪ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.
ለአላህ (ፈጣሪ) ቃል መገዛት የሕይዎት መስዋዕትነትን እስከመክፈል ድረስ ተገቢ መሆኑን ለሚያስገነዝበው ታላቁ የአረፋ በዓል እንኳን አደረሣችሁ፤ ኢድ ሙባረክ! የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በመላው ኢትዮጵያዊ በተደረገበት የማያቋርጥ ተፅዕኖ ምክንያት በዚህ ዓመት መጀመሪያ ከፍትኅ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎች መካከል ጥቂቶቹን መፍታቱ ይታወቃል። ሆኖም አሁንም ቢሆን ምንም ወንጀል ሳይፈፅሙ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የእሥር ጉሮኖ የሚማቅቁ አያሌ ሙስሊም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ስላሉ እነርሱ በሙሉ ከእሥር እስኪፈቱ ድረስ ሰላማዊ ተቃውሞው መገታት አይኖርበትም።
የትግሬ-ወያኔዎች ግፈኛ እና ዘረኛ አገዛዝ ባለፉት ዓመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመባቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አስታውሷቸው፤ ደማቸውም ደመ-ከልብ ሆኖ እንዳይቀር ድምፃችንን ለዓለም ማኅበረሰብ ከፍ አድርገን እናሰማ። የአረፋ በዓል ላጡ፣ ለነጡ ወገኖች ችሮታ የሚደረግበት በዓል ነውና፣ በዚህ የጉግ-ማጎግ አገዛዝ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ለሚፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰብዓዊ የዕርዳታ እጆቻችሁን ዘርጉላቸው። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በዓሉ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የታላቅ ተስፋ ዕለት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ኢድ ሙባረክ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት