የሕወሓት መንግስት የአውሮፕላን አብራሪውን ኃይለመድህን አበራን መኪና ለጨረታ አቀረበ

September 14, 2015

(ሪፖርተር) በጥር 2006 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ንብረት የሆነች የቤት መኪና በሐራጅ ለጨረታ ቀረበች፡፡

የሰሌዳ ቁጥር አአ 2-A32521 መኪና ጨረታ ያቀረበው ዘመን ባንክ ነው፡፡ ረዳት አብራሪው ለመኪና ግዢ ከዘመን ባንክ የተበደረው ብድር ስላልተከፈለው ባንኩ ተሽከርካሪዋን በጨረታ ለመሸጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ተሽከርካሪዋን ለጨረታ ያቀረበው በሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 261,503.37 ነው፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን መኪናዋን የገዛው ከአውሮፕላን መጥለፉ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኃይለ መድኅን ስዊዘርላንድ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቅም የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት ፍርድ ቤት አንድ ጊዜ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ ለስዊዘርላንድ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቶ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌለበት 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡

Previous Story

የቴዲ አፍሮ ምኞቶች

Next Story

ሞላ አስገዶም ከኤርትራ የከዱት ከሰባቱ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ብቻቸውን በስምንት ላንድ ክሩዘር ከወታደሮች ጋር መሆኑ ተገለጸ፣ አገዛዙ አስቀድሞ ግንኙነት እንደነበረው መግለጹ ለሞራሉ የፈጠረው መሆኑም ተጠቆመ፣ የህወሓት ባለስልጣናት ሲያደርጉት የቆዩትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በደህነቱ መ/ቤት አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማጥቃት መሸጋገራቸው፣ በአገር ቤት የበዓል ገበያው ማሻቀብና የነገሰው ውጥረት መላ ካልተበጀለት አገሪቱን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊከት ይችላል መባሉ፣ የመንግስታቱ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ የውጭ አገር ሰዎች ያወጣው ማስጠንቀቂያ፣ ቃለ መጠይቅ ከቴዲ አፍሮ የፌስ ቡክ ኮንሰርት አዘጋጆች አንዱ እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በአገር ቤት ስላለው ሁኔታ እና ሌሎችም

Go toTop