የቀድሞ የምዕራብ አፍሪካዋ ቻድ አምባገነን ሂስኒ ሀብሬ በእስር ዋለ

July 20, 2015

 

የቀድሞ የምዕራብ አፍሪካዋ ቻድ መሪ የነበረውና “የአፍሪው ፒኖቼ” ተብሎ ይታወቅ የነበረው ጨካኙ ሂስኒ ሀብሬ ለፍርድ እንዲቀርብ በሴኒጋል መንግስት ተያዘ።ፒኖቼ እንደ ሃብሬ በቺሌ ደቡብ አማሪካ ሰላማዊ ህዝብ በመጨፍጨፍ ይታወቅ የነበረ ነው።

ሂስኒ ሀብሬ በመፈንቅለ መንግስት ከተወገደ ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት በሴኒጋል በጥገኝነት ኖርዋል። ሂስኒ ሀብሬ የተከሰሰው በኢሰብአዊ ድርጊት መፈጻምና ሰቆቃ ነው። የቀድሞው አምባገነን ፍርዱን እየጠበቀ ነው።ሀብሬ እአአ 1990 መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መውረዱ ይታወሳል።

ሁማን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት ሂስኒ ሀብሬን ለአርባ ሺህ ሰዎች ሞት አላፊ ያደርገዋል።በስልጣን የቆየው ክ1982-1990 እአአ ነው።ከስልጣን ያስወገደው የዛሬው ቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዳቢ ኢትኖ  የሀብሬ መያዝ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ነው “ከክፋትና ከአባገነንነት ነጻ የወጣች አፍሪካ” ሲል ተናግሯል። ሂስኒ ሀብሬ ክሱን ክዷል።

ይህን ያህል ዓመታት የሴኔጋል መንግስት የሂስኒ ሀብሬ ፍድ መቅረብ ሳይፈቅድ ቆይቷል።በሴኔጋል ፍርድ ቤት ሀብሬ መቅረቡ አዲስ ምዕራፍ ከፋች ይሆናል። እስተዛሬ የአፍሪካ አምባ ገነኖች በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ብቻ ነው ሲቀርቡ የነበሩት።ባለፈው ዓመት የተባበሩት መንግስታት ፍርድ ቤት (UN’s International Court of Justice) የሴኔጋል መንግስት ሀብሬን ለፍርድ እንዲያቀርበው አዝዞ ነበር። የየሴኔጋል መንግስትና የአፍሪካ አንድነት ሂስኒ ሃብሬ ለፍርድ መቅረቡ ላይ ስምምነት ተፈራርመው ነበር።

ሂስኒ ሃብሬ በቤጂየም ፍርድ ቤት ይፈለጋል በማለት አል ጃዚራ አትቷል። የቤልጂግ ዜግነት ያላቸው ቻዳውያ በቀረቡት ኢሰብዓዊ ወንጀል ተፈጽሞብናል በማለት።

Previous Story

Hiber Radio: የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ትግሉን በአካል መቀላቀል ሰፊ መነቃቃት መፍጠሩና የአገዛዙ ደጋፊዎች ድንጋጤ፣ በዶ/ሩ ጉዞ የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ትንታኔ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሁለት መኪናዎች ውስጥ የተደበቁ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋል፣መድረክ ፕ/ት ኦባማ በጉብኝታቸው ወቅት እንዲያናግሩት ጥያቄ ማቅረቡ፣የአቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አጠራጣሪነት፣ አንድ ወታደር ሶስት ኮሌኔሎችን ገድሎ በርካቶችን አቁስሎ ራሱን ማጥፋቱ ፣ ካናዳ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዜጋዋን ችላ ማለቷ ማስወቀሱ፣ ገንዘቤ ዲባባ የእህቷን ሪኮርድ ለመስበር ፍላጎቷን መግለጿ፣ የዑበር የ7.3 ሚሊዮን ዶላር መቀጣትና ሌሎችም

Next Story

” የምታስፈራው የታማኝ ኢትዬጲያ!” – ከኤርሚያስ ለገሰ

Go toTop