ፕረዚዳንት መንግሥቱ ሀይለማርያም የት የተወለዱት??

February 3, 2025

ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በ1927 በዎላይታ በዳምታ ሶሬ ወረዳ የተወለደ በእናትም በአባትም ወላይታ ነው። ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ሀይለማርያም በወላይታ ተወልዶ ያደጉ የወላይትኛ ቋንቋ ጥሪት የሚናገሩ በሕይወት እያሉ አንዳንዴ አማራ ነው፣ አንዳንዴ ኦሮሞ ነው፣ ሌላ ጊዜ ከፋ ነው ይላሉ። ይሄ ሁሉ የኔ ነው የኛ ነው የሚል ሽሚያ ከምን የመነጨ እንደሆነ አይገባንም።

ማንም ምንም ብልም ይህ ምርጡ የዎላይታው ኮከብ በፊውዳል አገዛዝ ወደ ኋላ የቀረችውን ሃገር ኢትዮጵያ ፊውዳል አገዛዝን በመገርሰስ ሀገርቷ ወደ ፊት ጉዞ ያስጀመረ ምንም እንኳን ብዙዎች ቢሞቱ እና ቢጎዱም ሃገር የመራ የመላው አፍሪካውያንን የነፃነት ትግል የደገፈ የጥቁሮች መከታ የእኩልነት ቀንዲል የለውጥ አራማጅ አብዮተኛ ድንቅ መሪ ነው።

ኢትዮጵያ ያለ ዎላይታ ምንም ናት ነገር ግን ወላይታ ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ ለሀገር ክብር፣ ለሉዓላዊነቷ እንዲሁም በሀገርቷ ሽግግር ፖለቲካ ውስጥ ቀዳሚ መሃንዲስ ዎላይታ መሆኑ ሰማይ ምድር የማይክደው ሀቅ ነው።

ዎላይታ ለዚህች ሀገር ብዙ ሥራ ሰርቷል፣ ብዙ ዋጋና መስዋዕት ከፍላለች። ኢትዮጵያ ለወላይታ የሚትከፍለው ብዙ ዕዳ አለባት።
ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ሀይለማርያም የኢትዮጵያ ዘውዳዊ አገዛዝ በመጣል በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲ ስርዓት በመዘርጋት ሀገሪቱን ከ1966 እስከ 1983 ድረስ ለ17 ዓመታት የሀገርቷን ሉዓላዊነት እና ክብር ሳያስደፍሩ የመሩ ለሁሉም አፍርካዊያን ምሳሌ የሚሆኑ ጀግና መሪ ናቸው።

ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በ1927 በዎላይታ መወለዳቸውን እንኳን ታዋቂው የአለምአቀፉ ሚዲያ ቢቢሲ ከ18 ዓመታት በፊት በሰራው ዝርዝር ዘገባውን እያመለከተ እያለ የኛዎቹ ግን አንዴ አማራ ነው፣ አንዴ ኦሮሞ ነው፣ አንዴ ከፋ ነው እያሉ ገና ከወዲሁ ታሪክ ለመቀማት ይጣደፋሉ።
ሙሉ ዘገባው Link ከታች በአስተያየት መስጫ ተቀምጧል። በርግጥ ፕሬዚዳንት መንግስት ሀይለማርያም የሀገርቷ በሚመራበት ጊዜ ለአንድ ብሄር ያላዳላ፣ ማንንም በአንድ አይን የሚመለከት ደንቅ መሪ ስለሆነ የራሱን ብሄር መግለጽ አይፈልግም።

ለመሆኑ በኢትዮጵያ ለምንድነው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች የወጡበት ብሄር እና አከባቢ ላይ የይገባኛል ሺምያ እና ክህደት የሚበዛው ይላሉ ?

ዜና ወላይታ

1 Comment

  1. ዜና ወላይታ ወንድሜ ማንም አልተሻማህም አትስጋ ብሮ ያንተው ይሁን ብቻ ከላይ ዲሞክራሲ ያመጡ ላልከው ብዙዎቹ ከተስማሙበት እኔ ግድ የለኝም መቼም የማንሰማው ጉድ የለም እሱ ያደረሰው በቤትህ ይድረስ አልልም ምክንያቱም ረጋሚ ተደርጋሚ ይባላልና። ሓይለ ማርያም ደሳለኝም ነበረልህ እኮ ደምረህ ብትሰቅለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ይቅር ብየሃለሁ

Next Story

አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ ባሕርዳር ውስጥ በታጣቂዎች ተገደሉ

Go toTop