“ባለፉት ስድስት ዓመታት አንድም ሰው ‘torch’ አላደረግንም – የሞቀ  ጭብጨባ፡፡” ነፃነት ዘገዬ

February 2, 2025

ይህ ማይም ሰውዬ በስንቱ አሳቅቆ ሊፈጀን እንደሆነ ቀጣዮቹን ምሣሌዎች እንመልከት፡፡

Torch – ትርጉሙ flashlight/ባትሪ ወይም በገጠር አካባቢ ከጣሊያንኛ ተወስዶ ‹ላምባዲና›  የምንለው ነው እንጂ እርሱ ማለት የፈለገው ከእግሊዝኛ ወደአማርኛ ሲመለስ “ማሰቃየት” የሚለው አይደለም፡፡ ይህን የእንግሊዝኛ ቃል በዐረፍተ ነገር ብናየው – He broke his torch when he fell down. Please give me that torch; I want to use it when I have to go to the rest room because the bulb doesn’t work there.

Torture – ትርጉሙ እንደስም “ስቃይ”፣ እንደግሥ ደግሞ “ማሰቃየት”ን በሰው ወይ በእንስሳ ላይ መተግበር ማለት ነው – ማሰቃየት አርዕስታዊ ስም ነውና፡፡ ምሣሌ፡- The pathological liar Abiy Ahmed tortured millions of Ethiopians in the past six years, though he blatantly denies it.

ይህ ሰው ውሸቱ ብቻ ሣይሆን ሳያውቅ አውቃለሁ ባይነቱ ከዕብለቱ ባልተናነሰ የሚያቃጥለን ሰዎች ጥቂት አይደለንም፡፡ የግል ትምህርት ቤት የኬጂ ተማሪ የማይሠራቸውን አንድ ሁለት ያህል የእንግሊዝኛ ስህተቶቹን እንይለት፡፡

Both country – to mean both countries;

By implies – to mean by implication;

 

ወደ ዋናው ቁም ነገር እንግባ፡፡ ይህ ሰውዬ ከኢድ አሚን ዳዳ በላቀ የድንቁርና ኩራቱ እየተኮፈሰ የሚመራው የብል.ግና ፓርቲ – ፓርቲ መባል እንኳን የለበትም ነበር – ከትናንት ጀምሮ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ይህ ሰውዬ ከዓለም ህጎች በሙሉ በሚጣረስ መልኩ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ጠቋሚ፣ ራሱ አስመራጭ ሆኖ ራሱን እንደሚያስመርጥ ባለፈው ስብሰባ ታዝበናል፡፡ እኛስ እኛ ነን፡፡ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬው ስለዚህ ዋሾና አፈንጋጭ ዕብድ ፀጥ ረጭ ማለቱ የሚገርም ነው፡፡ አሁንም 2000 የሚጠጋ ከብቶችን ማለትም ድልብ ሠንጋዎችን ሰብስቦ በዐድዋ መታሰቢያ አዳራሽ እየወሸከተ ነው፡፡ በርዕሳችን የተጠቀሰው ፍጹም ውሸት በዚህ ሰውዬ አንደበት የተነገረው እንግዲህ በትናንታው ዕለት በዚያው ጉባኤ መሆኑ ነው፡፡ የርሱ ውሸት እንዳለ ሆኖ በእያንዳንዱ የውሸት እስትንፋሱ የሚስተጋባው ጭብጨባ ደግሞ ከማበሳጨት አልፎ በነማን እየተገዛን እንደሆነ ሲያስቡት ዕበዱ ዕበዱ ያሰኛል፡፡ እሱስ ሀፍረቱን ባወጣ ሸጦ በልቷል፡፡ ያ ሁሉ ሰው ግን እንዴት አንድ ይሆናል? ነገ መኖሩን እንዴት ረሱ? ለትውልዳቸው ማሰብስ እንዴት አቃታው? ይህ ጊዜ እኮ ያልፋል፡፡ ያኔ “ ተመልከት ያን ልጅ! የማን ልጅ እንደሆነ ታውቃለህ? የወሽካታው አቢይ ፓርላማ እንቅልፋምና አጨብጫቢ ልጅ ነው!” መባል በእጅጉ አሣፋሪ ነው፡፡ ዘመድ ካላቸው ይህን የታሪክ ጠባሳ ይንገራቸው፡፡ ከዚህም ብዙ ሳይመሽ፡፡

ከጃዋር እስከ ሕዝቅኤልና ፀጋየ አራርሣ፣ ከሌንጮ ባቲ እስከ ምርኮኛ አሥር አለቃ ጁላ፣ ከመለስ ዜናዊ እስከ ጌታቸው ረዳ፣ ከአሥራት ገብሩ እስከ ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ከአልማዝ መኮ እስከ አልማዝ ሠይፉ፣ ከለማ መገርሣ እስከ ሽመልስ አብዲሣ፣ ከታዬ ደንደኣ እስከ ታየ ቦጋለ፣ ከመረራ ጉዲና እስከ በቀለ ገሪባ፣ ከኃይሌ ፊዳ እስከ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ፣ ከአቢይ አህመድ እስከ ለመ መገርሣ፣ ከኩማ ደመቅሣ እስከ አበበ ቶላ ፈይሣ፣ ከሲሣይ ጋጋኖ ማለትም አጌና እስከ ኃይሉ ጎንፋ፣ ጄኔራል ዋቄ እስከ አበቡ ደባልቄ፣ ከደበላ ዲንሣ እስከ ጫልቱ መገርሣ፣  … ምን አለፋህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በጉልበቱ ገብቶ የሚፈተፍት ወይም በምርጫ ተሣትፎ ሥልጣን የሚይዝ ሁሉ አፍ መፍቻ ቋንቋውን ጓዳው አስቀምጦ በአማርኛ እየተናገረና መጽሐፍ ጽፎበት እንጀራውን እያበሰለ አሁን ምን ታያቸውና ነው አማርኛን የማጥፋት የማይሆን ዘመቻ በዐዋጅ ያጸደቁት? አማርኛ በዋሽንግተን ዲሲ አንዱ የብሔራዊ ቋንቋ መሆኑን፣ በቻይናና በራሽያ በትምህርት በቤቶች ሳይቀር እየተሰጠ መሆኑን፣ በኮርያውያን አንደበት እየተንበለበለ መነገሩን፣ በብዙ ፈረንጆች አንደበት የአፍ መፍቻ ያህል እንደብርቅ መነገሩን፣  በጀርመን የማኅበራዊ ሣይንስ የጥናትና ምርምር ማካሄጃ ቋንቋ መሆኑን፣ በአፍሪካ እጅግ ብዙ ሀገራት ተፈላጊ መሆኑን፣ ወዘተ. እኚህ ደናቁርት ባለጊዜዎች አላወቁ ከሆነ ይነገራቸው፡፡ ባለቤቱ የሚያቀለውን አሞሌ ባለዕዳ የሚቀበልበት መልካምና የተለዬ ወይም ያልተጠበቀ አጋጣሚ መኖሩንም አማርኛን በማጤን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ያባረረቻቸውን አማሮች ዓለማችን ተቀብላ በብዙ በረከቶች እንዳጎናጸፈቻቸው ሁሉ ሕወሓት በከፊል ኦሮሙማ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋው የዘመተበትን የአማርኛ ቋንቋ ደግሞ ይህቺው ዓለም አላሣፈረችውም – በፀጋ ተቀብላዋለች፡፡ ወደፊትም ገና የዓለም አንዱ ቋንቋ ይሆናል፡፡ ይህን ስል ግን ከቋንቋ ዕድገት ህግና ሥርዓት ተነስቼ እንጂ ቋንቋውን ወይም ተናጋሪዎቹን ስለምወድ አይደለም – ደግሞም ለምንስ እጠላቸዋለሁና? በመልመድና በመማር ካልሆነ እንደቋሚና ተንቀሣቃሽ ንብረት ከእናት አባት የማይወረሰው ቋንቋ በመሠረቱ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ ዱላ መማዘዣ ሊሆን አይገባም፡፡ በቋንቋ የሚጣሉ እልም ያሉ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ ነገ ጥለሃት በምትሄዳት ዓለም ውስጥ የኔ የምትለው አንድም ነገር የለም – ሌላው ቀርቶ የኪስህ ቦርሣም ያንተ አይደለም፡፡ ስንቱ ነው በቢሊዮኖች አከማችቶ አይቶት ብቻ የተሰናበተ? በእውነት ቂልነት ነው፡፡ የአንድን ቋንቋ ተናጋሪዎች ልትጠላ ትችላለህ፡፡ ቋንቋውን መጥላት ግን ዕብደት ነው፡፡ አፄ ዮሐንስ በአማርኛ የገዙት፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም በአማርኛ የገዛው፣ አፄ ኻይለ ሥላሤ በአማርኛ የገዙት፣ አፄ ምኒልክ በአማርኛ የገዙት አማርኛን ስለወደዱት ሣይሆን ለአገዛዝ ስላመቻቸው ነው፡፡ እንግሊዝኛን በቦሌም በባሌም ልንማር የተገደድነው እንግሊዝን ወደን ሳይሆን እንግሊዝኛን መናገር የሚሰጠውን ዓለም አቀፍ ጠቀሜታ አስበን ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አማርኛ ባይኖር ኖሮ ይሄኔ ኦሮሙማ ጉድ ሆኖ ነበር፡፡ አንድ እውነተኛ ቀልድ ትዝ አለኝ – የኔ ነገር፡፡ “ጨዋ” አንባቢ ይህን አንቀጽ ይዝለለው፡፡

አባትና እናት ገላቸውን ለመታጠብ ወደፍል ውኃ ይሄዳሉ – ወንድ ሕጻን ልጃቸውን ይዘው፡፡ በዚያን ዘመን ወንድና ሴት በአንድ ላይ ወደአንድ መታጠቢያ ገንዳ አይገቡም ነበርና እናት ለብቻዋ አባትም ለብቻው ሊገቡ ሲሉ ልጁ ወደእናቱ ያዳላና ወደዚህ ልግባ ይላል – ወደእናቱ፡፡ አስተናጋጆች ደግሞ “ሴት ልጅ ወደ ወደእናቷ፣ ወንድ ልጅ ደግሞ ወደ አባቱ ነው የሚሄድ” ብለው ይከለክሉታል፡፡ ልጁ እየከፋው አባቱ ጋ ገባ፡፡ ቆመው መታጠብ እንደጀመሩ ሣሙናው ያዳልጠውና ወድቆ ሊፈጠፈጥ ሲል የአባቱን አንድ ነገር ይዞ ለጥቂት ይተርፋል፡፡ አባቱም “ይሄኔ እናትህ ጋር ገብተህ ቢሆን ኖሮ ጥርስህን ለቅመህ ነበር፡፡” አለው ይባላል፡፡ ነገር ያለማዋዣ አይጣፍጥምና ባለጌ አትበለኝ፡፡

እናሳ! “በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ” ብላችሁ ተቀኛችሁ?

ለማንቻውም የዕብዱ አቢይ ፀሐይም እየጨለመች ናት፡፡ ባትጨልምበት ኖሮ የሚናገረው ሁሉ ይህን ያህል ቅጣምባሩ ባልጠፋበት ነበር፡፡ የጨለመበት ሰው ደግሞ ልክ ባሕር ላይ እየሰመጠ ያለ ሰው ይመስላል፡፡ እየሰመጠ ያለ ሰው የሚያድነው እየመሰለው ዐረፋውንም ገለባውንም ይጨብጣል፡፡ እንጂ በየእሥር ቤቱ ካለበቂ ምግብ፣ ካለመብራትና ውኃ፣ ካለአየር በድብደባና ኢሰብኣዊ ድርጊቶች መከራና ሲቃ እየወረደበት ታጉሮ የሚገኘው ዜጋ ከአንድ ሰው አንሶ ነው እስከዚህ የሚበጠረቀው? የሚገርመው አጨብጫቢዎቹም እኮ እውነቱን ያውቃሉ – ለማጨብጨብ ስለሚገደዱ እንጂ፡፡ አማራን እንደሰው ሳይቆጥር እንደተናገረ እንውሰድለትና እነክርስቲያን ታደለንም እነዮሐንስ ቧ ያለውንም እንተዋቸው፡፡ እርሱና ቡድኑ እንደሰው ከሚቆጥሩት የኦሮሞ ነገድስ ቢሆን ስንቱ ነው የታሰረው፣ የተሰቃየው፣ በሌሊትም ወጥቶ በከተማ መሀል የተገደለው? ምን ዓይነት ፌዝ ነው?  ውይ … አሁንስ ምርር አለኝ፡፡

 

3 Comments

  1. እሱ ምን አጠፋ የሚያዳምጡት እንጅ፡፡ እንዲህ አይነት ስኳር ለመግዛት የማይታመን ሰው ከላይ ቁጭ ብሎ ሲጋልባቸው ለዚች ቀፈታቸው ሲሉ እንዴት ሌላው ቢቀር ማኩረፍ ይሳናቸዋል ልጃቸው ክርስቲያን ይህን ተጠይፎ ይማቅቃል እነሱ ይጎነበሳሉ እሱም አዛውንቶች እያለ የሚሰድበው እነሱኑ ነው፡፡

    • አየ Zubeda ካኳረፉና ማጨብጨብ ካቆሙማ ዘብጥያ ያወርዳቸዋል፡፡ ያገራች መረገም ግን ድንበር ማጣቱ ያሣዝናል፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ይህን መሠል አውሬ ወደ ሥልጣን ይወጣል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ መጨረሻችን እንደ አንድ የልቦለድ መጽሐፍ ያጓጓል፡፡ እሱ ይሁነነ፡፡

  2. ስናሳዝን። እንዴት ነው በምናባዊ ዓለም ራሳችን አስጠልለን ከእውነት የምንሸሸው? የሴራ እርካብ፤ የደም መንበር ጸሃፊ ፈጥሮ ነው የጻፈው? ከብልጽግና መከራ ያመለጡት ሁለቱ ጋዜጠኞች ከአስከሬን ጋር መታሰራቸውና እንግልት እንደደረሰባቸው እንባ እየተናነቃቸው ሲናገሩ ስለ ደርግ ወይም ሰለ ወያኔ ዘመን ሳይሆን የነገሩን ስለ ብልጽግና አይደለም እንዴ? በክልሎችና በአዲስ አበባ በየስርቻው የተቆለፈባቸው ሰዎች የሚደርስባቸውን መከራ ጠ/ሚሩ አያቅም? እስቲ አዋሽ አርባና በአፋር እስር ቤቶች የታጎሩትን ሂዶ ይጎብኝ። በአዲስ አበባ በተለያዪ ቦታዎች የተዘጋባቸውን ሰዎች በግልጽ ያናገር። አልተገረፍንም ይሉት ይሆን? ሰው በሜዳ ላይ ያለምንም በደል በጥይት ተደብድቦ በሚገደልበት በሃበሻዋ ምድር እንዲህ መመጻደቅ የጤንነት ሳይሆን የበሽታ ነው። ችግሩ የሞተውም ሆነ የታሰረው እየተረሳ ሰው ራሱን ለማሰንበት ሲሯሯጥ የእርሱም ወረፋ ይደርስና ወደዚያው ይጋዛል። በዚህ የተነሳ ሟችና ገዳይ ይዘነጋሉ። ዳኝነትና ፍትህም ገደል ይገባሉ።
    በንጉሱም ጊዜም ሆነ በደርግ፤ በወያኔም ሆነ በብልጽግና በዜጎች ላይ ግፍ እንደተሰራና እንደሚሰራ ጠንቅቀን እናውቃለን። የሚያሳዝነው ትሻልን ትቼ ትብስን መሆኑ ነው። አንድ ወዳጄ ጋር ስናወራ እንዲህ አለኝ። ሳይታሰብ ከ20 በላይ የሆነ የወታደር መንጋ ቤትክን ይወራል፤ ይፈትሻል፤ ይዘርፋል። ለመረጃ ያስፈልጋል ተብሎ ተመዘገበ የተባለው እቃህም ይረሳና ገቢያ ላይ ወጥቶ ሲሽጥ ታገኘዋለህ አለኝ። በዚህ ስልት የከበሩ ብዙ ናቸው። እቃ ጠፋብኝ፤ ወሰዳችሁ፤ እባካችሁ መልሱ ማለት ጭራሽ አይቻልም። ለማስመለስ ሙከራም ካደርክ አንድ ቢሮ ወደ አንድ ቀጠሮ እየሰጡ ስትመላለስ ልብህ ውልቅ ትልና ይህችን ዓለም ትሰናበታለህ በማለት በምሬት አጫወተኝ። በጉምሩክ፤ በፓስፓርትና በሌሎችም የህብረተሰብ መገልገያ ተቋሞች በዘርና በቋንቋ የተዋቀረው የኦሮሞ ስብስብ ከወያኔዎች በከፋ ሁኔታ ሃበሳህን ያስቆጥርሃል። ያስፈራራሃል። ኦሮምኛ ተናገር ይልሃል። ኸረ ስንቱ ብቻ በሃገራችን የማይደረግ የግፍ አይነት የለም። ሃገሪቱን እንመራለን የሚሉት ሰዎችና እውነት እየተላለፉ ግራ ተጋብተናል። መቼ ይሆን ይህ ህዝብ ይህች ሃገር የሚልፍላት? የሚያውቅ አንድም ሰው የለም።
    Tom Gardner – The Abiy Project: God, Power and War in the New Ethiopia በተሰኘው መጽሃፍ ላይ ጸሃፊው የሚያስነብበን በስልጣን ላይ ለመሰንበት ተብሎ በህዝቡና በምድሪቱ ስለሆነው መከራ አይደለምን? በሽታችን ምን ይሆን? የጭንቅላት ወይስ የመላ ሰውነት እክል?
    ጠ/ሚሩ ቶርች አላደረግንም ሲል ጥፍር አነቀልንም፤ የሰው ብልት ላይ ውሃ አላንጠለጠልንም፤ በኤሌክትሪክ ሾክ ሰውን አላሰቃየንም፤ ምስማር የተመታ ጣውላ ላይ ሰው እንዲረማመድ አላስገደድንም፤ እስረኛን ከሞተ ሬሳ ጋር አላሳደርንም፤ ጎሳ፤ ብሄርና ቋንቋ እየጠሩ ሰውን አላዋረድንም እያለን ነው። ለገባው ” Torture” የሚለው ቃል የሰውነትና የስነልቦና ሰቆቃንም ይጨምራል። በብልጽግናው መንግስት ሁለቱም በደሎች አልተፈጸሙም ማለት በ 120 ሚሊዪን የሃበሻ ህዝብ ላይ ማላገጥ ነው። የሚሻለው ጉዳዪን አምኖ ተቀብሎ ነገሮችን ለማስተካከል እንሰራለን ማለት ነበር። እየካድና እያስካድ የሄድት የቀደሙት ጠበንጃ ተሸካሚ አለቆቻችን ዛሬ ያሉበትን ማየት በራሱ ትምህርት በሆነ ነበር። ፈርዶብን እኛ ግን ከታሪክ አንማርም። ከጠላት ላይ ጠላት እያበዛን፤ ያዙን ልቀቁኝ እንዳልን ሳናስበው ተፈንግለን የማንነሳበት አወዳደቅ እንወድቃለን። መቼ ይሆን ሃበሻ ተሳስቻለሁ የሚለው?
    ጣሊያንን ከጀርመኖች ጎን አሰልፎ ህዝቡን ፋሺዝምን ያጠመቀው ሞሶሎኒ ጊዜው ሲደርስ ከሞትና በአደባባይ ከመዋረድ ያስጣለው የለም። የሚገርመው ከአካላቱ ክፍል አንድ እግሩ እስከ ዛሬ ድረስ ማን ገንጥሎ እንደወሰደው እንኳን አይታወቅም። የጎደለ አካሉ ነው ለቀብር የበቃው! ከእኛ በላይ ላሳር ያሉ መሪዎች ሁሉ አሳር አብልተው እነርሱም መጨረሻቸው ከፍቶ አፈር ተመልሶባቸዋል። Viktor E. Frankl, Man’s Search for Meaning በሚለው መጽሃፉ ላይ እንዲህ ይላል “For the world is in a bad state, but everything will become still worse unless each of us does his best.” መጽሃፉን ፈልጉና አንብቡ። የሰው መኖር የሚለካው ለሌላው መኖር ሲችል ነው። ሰውን ማሰቃየት ሙሉ ሥራችሁ የሆነ የጸጥታና የስለላ መረብ ወገኖች ሁሉ ልታውቁት የሚገባው ነገር ለእናንተም ጊዜ ይመጣል። ዋ በህዋላ እኔ የለሁም። ህዝብ አታሰቃዪ። ሰው መግደልና መግረፍ የመኖሪያ ብልሃት መሆኑ እንጀራቹሁን የደም እንጀራ ያደርገዋል። አቁሙ። ጠ/ሚሩም ልብ ግዛ በኢትዮጵያ አፈና፤ ግድያ እስራትና ማሰቃየት አለ። መሸፈጥ የፓለቲካ ጥበብ አይሆንም። ውድቀትን ያመጣልና በጊዜ ነገሮች ይስተካከሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አሳዛኙ የዶክተሩ ግድያና ከባዱ ውጊያ / በትግራይ የፌዴራል ሀይል እንዲገባ ተወስኗል? / በዐብይ ስምምነት የተፈፀመው የደሮን ጥቃት

Next Story

”የዶ/ር አንዱዓለም ዳኜ ገዳዮች የአገዛዙ ወታደሮች ናቸው” የአማራ ፋኖ በጎጃም

Go toTop