“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብስጭት መለሱ ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ለስም የሚከብዱና በጣም የሚከበሩ የክልል ርዕስ መስተዳደሮች ነበሩ ዛሬ ግን መድበኝ ስራ ስጠኝ እያሉ ይለምኑኛል ያንተ እጣ ፈንታ ከነሱ የባሰ ይሆናል አልሰራም የሚትል ከሆነ ለማኝ አደርጋለሁ ብሎ የሀገርቱ ባለሥልጣናትና የሁሉም ክልል ፕረዚዳንቶች በተሰበሰቡበት ወርፏቸዋል።

ወላይታ 


እኔን እና አቢይ አህመድን ልለየን የሚችል ከሞት ውጪ ምንም የለም ብሎ በተናገሩት አንድ ወር ሳይሞላው ለማ መገርሳ ቁም እስረኛ ሆኗል።

ለአቶ ለማ መገርሳ ያልሆኑት አቢይ አሕመድ ለማን ይሆናል? ለለማ ገርርሳ ያልታመኑት ጠሚ ሚኒስትር ለማን ታማኝ ይሆናል? ከለማ መገርሳ በላይ ለአቢይ ውለታ የዋለለት ሰው ማነው?

የወጣቶች ንቅናቄ


 

2 Comments

  1. ሲያንሰው ነው ይሄ ማይም አሽቃባጭ፡፡ ሰው ነኝ የሚል በሰው አምሣል የተፈጠረ ሰው ከዚህ በሰይጣን ልኬት ከተሠራ በላዔሰብ ጋር እንኳን ሊሠራ አንድም ደቂቃ አብሮ አይቆይም፡፡ አቢይ ያልበላው የለም፤ ትንሽ ዕድሜ ካለችው ገና የቀረነውንም እንክት ያደርገናል፡፡ የሰው ሥጋ በልቶ የማይጠግብ ሆድና የሰው ደም ጠጥቶ የማይረካ ፍላጎት ሰጥቶታል፡፡

  2. የሃበሻ ፓለቲከኞች ጨካኞችና ርካሾች ናቸው። ህልማቸውም የቁም ቅዥት ነው። የሚናገሩትን የማይኖሩ፤ ለራስ ሲቆርስ የማያሳንሱ፤ ባጭሩ ከጊዜው ጋር ሮጠውና አሯሩጠው እንደ ጧት ጤዛ የሚጠፉ ናቸው። ጠ/ሚ አብይ ይህን ተናግሮ ከሆነ እሱን ከመንግስቱ የሚለየው ነገር አለመኖሩን ያሳያል። መንግስቱ በሄደበት ሁሉ የወታደራዊ አዛዦችን ሆድ በድላው እየነካካ ቀፈታም ሆዳም በማለት ተራ ዘለፋ ያደርስ እንደነበረ በህይወት ያሉ የሚመሰክሩት ነው። ጭካኔአችን ከሰው ተርፎ ለእንስሳትም የሚተርፍ ነው። ጅራቱን በሰላም የሚያቋላን ውሻ ተኩሶ የሚገድል፤ የቆሙ ከብቶችን በመትረጌስ የሚጨፈጭፍ የቁም እብዶች ያሉባት ሃገር የሃበሻዋ ምድር ናት። መለሰ ብለን ያለፈውን ታሪካችን ስንመለከትም ከዚህ የከፋ እንጂ የተሻለ ታሪክ የለንም። ግን ለምን ይሆን እንዲህ ያለ ጨካኝና አረመኔ የሆነው?
    ደርግ የወሎን ረሃብ አስታኮ ንጉሱን ለማጥላላት ያለ የሌለውን ነገር አዳምሮ ውሻቸውን ሲያበሉ፤ ለልደትና ለሌላም ኬክ ሲቆረስ የነበረን የቆየ ፊልም ከወሎው ረሃብ ጋር እያዛመደ ስማቸውን አጠልሽቶ አፍኖ በመግደል ቀበራቸው። ልብ ላለው ግን ደርግ የፓርቲ ምስረታ በማለት አዲስ አበባንና ዙሪያዋን ሲያሽሞነምን በወሎ፤ በሽዋ፤ በትግራይና በጎንደር ያለቀው ህዝብ ቁጥር በንጉሱ ዘመን ካለቀው 5 ጊዜ እጥፍ ይሆናል። ስናሳዝን። ካለመግደል ሌላ ሙያ የለንም። ስድቡ፤ ዘለፋው፤ ቋንቋዬ ብሄራዊ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ ማለቱና ኡኡታው ኸረ ስንቱ! የግፉ አይነት ብዙ ነው። እስቲ ከወያኔ የመከራ ዝናብ ውስጥ “ሞቶ መነሳት” የሚለውን የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ታሪክ አንቡት። እናት ያለው ሰው እንዲያ በእናት ላይ ይጨክናል? ሃይማኖቱ፤ ምህላው፤ ስለቱ፤ መርፌ ወግቶ ያን ግደል ይህን አሰንብትልኝ ማለቱ ሁሉ እይታችን ምን ያህል እንደተጣረሰ ያሳያል። ሌላ ትርጉም የለውም። ችግራችን የጭንቅላት እንጂ የዘር፤ የክልል ወይም የቋንቋ አይደለምና! የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገናል፤ እሱም የማይገኝ ሃብት ሆኗል። አቶ አረጋ ከበደን ጠ/ሚሩ ይህን አሉት አላሉት ጉዳዪ ኢምንት ነው። ችግሩ የእንዲህ አይነት ጠርዝ የረገጠ ጀብደኝነት ምንጩ ምንድን ነው? እሱን ነው ያልደረስንበት። የማይድን በሽታ!
    ደርግ ንጉሱን ከስልጣን ባወረደ እለት ውሻቸው አጠገባቸው ነበረች። ጥጋበኛው የወታደር መንጋ ንጉሱን ወደ ቮልስዋገኗ ሲያስገባ ውሻዋም አብራ ለመግባት ስትሞክር በእርግጫ ተመታ ስትጮህ ይስቁ ነበር። ያ ሁሉ ወሮበላ የወታደር መንጋ ዛሬ በህይወት የለም። ጨካኞችን ጨካኝ ይገጥማቸዋል። ለእንስሳት ልብ የሌለው ሰው ለሰው ልጅ ይራራል ተብሎ አይታመንም። የዛሬው አለቆቻችንም ሆኑ ተመልሰው አለቃ ለመሆን ከወደ መቀሌ ሃተፍ ተፍ የሚሉት ወይም በየስፍራው ጠበንጃ አንግተው ህዝባችን የሚያሰቃዪት ሁሉ ጊዜ ከንቱ ያደረጋቸውና የሚያደርጋቸው የሙት ስብስቦች ናቸው። ትዕቢት ውድቀትን የሚቀድመው ለዚህ ነው። ማንም ይሂድ ማንም ይምጣ፤ በሃበሻ ምድር ስላም አይኖርም። ጊዜ የሰጠው ይህንም ያንም አራኩቶ፤ ከእርሱ በፊት የነበረውን አጥላልቶና የቆመን አፍርሶ እሱም ፈራሽ ሆኖ ፍጻሜው ይሆናል እንጂ። አብይ አንተን ለማኝ አድርግሃለሁ ብሎ ከሆነ አቶ አረጋ ከበደ ደስ ሊለው ይገባል። ሞቶ የማያልቀውን ሰፊውን ህዝብ ይቀላቀላልና! እንኳን ደስ አለህ ብለናል!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

Next Story

ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ለአገው ፈረሰኞች በዓል መልክት አስተላለፈ!

Go toTop