ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡
ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ መጠን ከፍ እንደሚል አምናለሁ፡፡ ግሎባል አላያንስ፤ ቤተ አማራና ሌሎች የሚያደርጉት መዋጮ ተስፋ ይሰጣል፡፡ እንድረስላቸው፡፡ ከአክብሮት ጋር፤ አክሎግ
ምነው አምላክ ሆይ ይህን ያህል ጠላኸን፤ ተጠየፍከን፡፡ የሠራሃትን አገር፣ የፈጠርከውን ሕዝብ ለሠራዊተ አጋንንት አጋልጠህ መሠወርህ ለምን ይሆን? ምን እስክንሆን ነው ለኦነግሸኔ የመከራ ውርጅብኝ አጋልጠህ የተውከን?
አዲስ አበባ እየጠፋች ነው፡፡ ሕዝቧ ብቻ ሣይሆን ታሪኳም ቅርሷም ቅርጿም ወዳልነበርነት እየተቀየሩ ነው፡፡ አንበሣ አውቶቡስ መልኩንም ስሙንም ቀየሩት፡፡ አመልካች ሥራ ፈላጊዎችን በአማርኛና ኦሮምኛ ፈትነው የኦርምኞቹን ሲያሣልፉ ያማርኞቹን ጣሏቸው፡፡ አቤት ግፍ! የኑሮ ውድነቱን ከጣራ በላይ ሰቀሉት፡፡ ቤቱን የሚያፈርሱበትን የአዲስ አበባ ኗሪ ለማፍረሻ ገንዘብ ያስከፍሉታል፡፡ ካልከፈለ ዕቃውን ይቀሙታል ፤ አፈናቅለውም የትም ይጥሉታል፡፡
እነዚህ ወፍዘራሾች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየከመሩበት ያለው ከፍሎ የማይዘልቀው የታሪክ ዕዳ ከአሁኑ ያሣስበኛል፡፡ አይነጋ መስሏቸው በተለዬ እሽቅንድር አድርጓቸዋል፡፡ ጥጋብ ትቢታቸው ይሠሩት አሳጥቷቸዋል፡፡ የዕብሪተኞችን መጨረሻ ከደርግና ከወያኔ ሊማሩ አልቻሉም፡፡ የሁሉም ነገር መፍትሔ ጥይት ብቻ መስሏቸው ሕዝብን በጥይት አረር እየቆሉ አገር ማፍረሳቸውንና በተለይ አማራን መጨፍጨፋቸውን፣ ማፈናቀላቸውን፣ ማሳደዳቸውን፣ አግቶ ብዙ ገንዘብ ማስከፈላቸውን … በስፋት ቀጥለዋል፡፡ ያቺ ቀጭን የፍርድ ጊዜም አትቀርም፤ እየመጣችላቸው ነው፡፡ ያኔ ነው ጉዱ፡፡ ትልቁ ችግር የዐረመኔ አምባገነኖች ዳፋ ወይም ጦስጥምቡስ ለየዋሁ ዜጋ መትረፉ ነው፡፡
ኦነግሸኔ አቢይና ሽመልስ ሆይ! ሌላ የምላችሁ የለም፡፡ መልካም የግድያና የውድመት ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ ወደአባታችሁ ቤት ወደ ሲዖል እስክትሸኙ አባታችሁ ሣጥናኤልን ቶሎ ቶሎ አስደስቱ፡፡ ከምታፈሱት የአማራ ደም ጅረት ደግሞ እያንደቀደቃችሁ ጠጡ፤ ሥጋውንም ብሉ፡፡ የቀረቻችሁን አጭር ጊዜ በደምብ ተጠቀሙባት፡፡ ግን ይብላኝ ለልጆቻችሁና ለቀሪው ምሥኪን ኦሮሞ፡፡
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡
Ynegal Belachew
መቼ ይወድቅ ይሆን?እስከዚያስ
ስንቶቻችንን ይጨርስ ይሆን?pic.twitter.com/VVw9gRYGxJበዚህ ብቻ ፤ የአብይ መንግሥት አንድ ቀን ሥልጣን ላይ መቆየት አልነበረበትም!ምን ነካን?
— “I swear I will never be Amhara Again “ (@MulugetaGetah10) December 27, 2024
ሰማ ወዳጄ እግዜሩ የሃበሻን ምድር ከለቀቀ ቆይቷል። ግን የት ሄደ ብለህ አትጠይቀኝ። የህዝባችን ሰቆቃ አፍላቂዎች እኛው ራሳችን እንጂ ከሰማይ የመጣ ችግር ዛሬም ያኔም አልነበረም። ግን ያው በፈጣሪና በሰይጣን ላይ ነገር ማላከኩ የተለመደ ሆኗል። ለ3ሺ ዓመት ሲጠሩት አቤት የማይል ነገር ዝም ብሎ “ሰማዕኒ” ማለት መጃጃል ነው። የወሎ ረሃብ ያለፈውም ሆነ የአሁኑ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮዋዊ ነበር። ግን ያንንም ቢሆን ብናብር፤ ብንረዳዳ፤ ቀደም ብለን ብንነቃ ልንገታው በቻል ነበር። የዛሬው ደግሞ በብሄር ነጻነት የተሳከረ፤ በክልል ፓለቲካ የጠነበዘ ለሰው ልጆች ደህንነት የማይገደው የፓለቲካ ስብጥር ባለበት ዘመን ራስን ማየት ትተን ክራራይሶ ማለቱ ተንጋሎ መትፋት ይሆናል። አምናለሁ ይህን በማለቴ በድንጋይ ሊወግሩኝ የሚሹ እንዳሉ። ሲያምራችሁ ይቅር አትችሉም። የህዝባችን ገመና እናውቅልሃለን የምንል በቅርብና በሩቅ ያለን እኛው ራሳችን ነን። ሌላ ሰማያዊ ወይም ምድራዊ ሃይል የለም!
ትምህርት ቤት ዘግቶ፤ መንገድ ዘግቶ ለምኖና ቀምቶ እየበላ አማራን ነጻ አወጣለሁ የሚለው የፋኖ ክምችት አንድ የችግሩ ሃረግ ነው። በወለጋ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ነኝ እያለ ሰውን ቤት ዘግቶ በእሳት የሚያንቀለቅለው የሙት ስብስብ የህዝባችን መከራ አዝናቢ ሌላው ተባይ ነው። እነዚህና መሰል ሃይሎችን እደመስሳለሁ በማለት በምድርና በአየር እሳት የሚለኩሰው የብልጽግና መንግስትም ሌላው የመከራው ተደራቢ መከራ ነው። እነዚህ ሃይሎችና እንዲሁም በከተማና በገጠር ተወሽቀው በማታለል፤ በማጭበርበር፤ በመግደልና በማሰር ሌላውን እያስለቀሱና እያስወገድ ከጊዜው ጠበንጃ አንጋቾች ጋር በመተባበር ህዝባችን የሚመዘብሩ ሁሉ የህዝባችን መከራና ስቃይ አባዥዎች ናቸው።
አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ አማርኛውን ወደ እንግሊዝኛ እንድመልስ አስተርጓሚ ሆኜ ቆምኩ። አማርኛ ተናጋሪው ሃረር ተወልዶ ወሎ የኖረ በመሆኑ የሁለቱን የአማርኛ ቃና ቀይጦ አማርኛው እንዳለ ለገባው ያስቃል፤ ያዝናናል። በዚህ መካከል “ከመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል” የሚል ቃል ተናገረና እኔም ትርጉሙን “You snooze you lose” በማለት ተርጉሜ ሰውየው ተናግሮ አበቃ። ከስብሰባው በህዋላ አንድ ሃበሻ ጠጋ ብሎ ምን ቋንቋችን ታበላሻለህ አለኝ። እኔም በትህትና የቱ ላይ ነበር የተበላሽው ስል ከላይ ያልኩትን ጠቅሶ ወቀሳ ሰነዘረ። ወዳጄ አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ምን ብለህ ትተረጉመው ነበር ስለው። አሰበ አሰበና አላውቅም አለኝ። በማታውቀው ጉዳይ የክርክር አርእስት አትክፈት በማለት ተለየሁት። ስብሰባው እርዳታ ስለማሰባሰብ ነበር። በማናውቀው፤ አማራጭ ማቅረብ በሚሳነን ነገር ልክ እንደ አዋቂ እየቀረብን ነገርን ባናማታ ምንኛ ችግራችን በተቀረፈ። ግን ያን ከማድረግ ይልቅ ሌላው ላይ እጣት መቀሰርና ፈጣሪን ለምን ዝም አልክ ማለት ይቀናናል። በዚህም የተነሳ ለውጥና ሪፎርም እያልን ራሳችን ስንደልል፤ የብሄር ነጻነት ብለን ባርነትን ስናነግስ፤ ድል ሳናደርግ ጎራው ስንል ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች። እድሜአችንም እንዲሁ ይከንፋል። ዝንተ ዓለም እንኖር ይመስል በመሸ ሰአትም ሰውን ከመበደልና ተንኮል ከመስራት አንቆጠብም። የፈጣሪን ስም እየጠሩ የዘረፉ፤ የገደሉ ስንቶች ናቸው? ሃይማኖት የመነገጃ መሳሪያ እንጂ ለህዝቦች አንድነትና ህብረት መፍትሄ ሰጥቶ አያውቅም። ዛሬ በእኛም ሃገር ይሁን በመካከለኛው ምስራቅ ላለው መፈናከት ሃይማኖትና የሃብት ክፍፍል ዋናው መሳሪያ ነው። ስለዚህ ፈጣሪን ሳይሆን ተፈጥሮ ያደለንን ጭንቅላት ተጠቅመን በቻልነው ሁሉ ለህዝባችን ለመድረስ እንጣር። ሌላው ሁሉ ዝም ብሎ ጊዜ ማባከን ነው። እግዜሩም አርፎ ይተኛበት።
እግዚአብሔር ሁሌም በዙፋኑ ላይ ነው፣ እኛ ነን እሱ ካስቀመጠን ቦታ ጠፍተንና ሌላ ቦታ ሄደን እግዜር የጠፋ የመሰለን እንጂ እሱ ሁሌም በቦታው ነው። ወንድሜ የጠፋኸው አንተ ነህ፣ ወደቦታህ መመለስ ያለብህም አንተ ነህ
ኩኩዬ እንዲነጋልሽ ተፈጥሮንና ዙሪያሽን ተመልከች። የምድርን በራሷ ዛቢያ መሽከርከር አትርሺ! እኛ ነን ካስቀመጠን ቦታ የጠፋነው ላልሽው ባህላዊ አባባል ስለሆነ እውነትነት የለውም። የጠፋኸው አንተ ነህ ለምትይው እስከማውቀው ድረስ እኔን ፍለጋ የወጣ ሰው የለም። እንድፈለግም አልፈልግም። ከቦታየም ንቅንቅ አላልኩም። ይልቅስ ራስን ፈትሾ ፈጣሪን ለቀቅ አርጎ በታደለን ጭንቅላት ሁሉን መርምሮ ለምን ይሆን ችግራችን ዘመን ተሻጋሪ የሆነው? ለምነንም ሆነ ቀምተን በቃን ማለት ያልቻልነው በማለት ራስን ጠይቆ መፍትሄ መፈለጉ መልካም ይመስለኛል። መኖር የሚለካው በማይኖርበት ሃይማኖት በመመጻደቅ ሳይሆን መኖር ያልቻለውን በተግባር በመደገፍ ነው። ይታይሽ የተራበ ብቻ አይደለም የሚቸገረው። በውጭም በውስጥም የሞላለት የሚያባላው ያጣም ችግረኛ ነው ለተገለጠለት። በይ በእነዚህ ስንኞች ልሰናበትሽ።
ነጋ አልነጋ ብሎ ሰው ይራወጣል
አንደኛ ተጠልፎ ሌላኛው ይሮጣል
መርመስመስ መቧጠጥ እጣችን ሆነና
ቤሳ ቢስቲ ሆነ የትርፋችን ዋጋ
ለሚቀጥለው ቀን ደግመን እንድነቃ
ኩኩሉ እንላለን በድቅድቅ ጨለማ!