አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ዘጠኝ ኦርቶዶክሳውያን አማኞች ተገድለው ማደራቸው ተሰማ

November 29, 2024

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌ ፈረንቀሳና ሶሌ ጡጃ ቀበሌ ኅዳር 19 ለኅዳር 20 አጥቢያ ከሌሊቱ 8፡00 ገደማ በአንድ ቤተሰብ ዙሪያ ያሉ ዘጠኝ ሰዎች ተገድለው ማደራቸውን እናት ፓርቲ ይፋ አድርጓል።

ከሟቾቹ መሐል 70 ዓመት ያለፋቸው ሁለት አረጋውያን አባቶች እንዳሉ ያስታወቀው ፓርቲው በእድሜ የገፉ እናቶችና ወጣቶችም አሉበት ብሏል፣ የሟቾች ስም ዝርዝርም ደርሶኛል ብሏል።

“ጭፍጨፋውን በአካባቢው ሰዎች አጠራር ‘የጫካው ሸኔ’ እንዳደረገው እርግጠኛ እንደሆኑ የሚናገሩት ነዋሪዎች ሌሊት ላይ መጥተውና እየመረጡ ወንዝ ዳር ከወሰዱ በኋላ አስተኝተው ጭካኔ በተሞላበት መልኩ እንደፈጇቸው ገልጸውልናል” ያለው እናት ፓርቲ ባደረገው ማጣራት ከሟቾች በተጨማሪ አቶ ገነነ ተካልኝ፣ መ/ር ካሳሁን እሸቱ፣ አቶ አበበ አሰፋ እና አቶ ሽብሩ አሰፋ የተባሉ ግለሰቦች ታግተው እንደተወሰዱና እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በምን ኹኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማያቁ ለመረዳት ችለናል ብሏል።

ከሰሞኑ በዚሁ አካባቢ 2 ሰዎች ተገድለው ሌሎች 8 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ ከአካባቢው ሰምቻለው ያለው ፓርቲው ታጋቾቹ የትና በምን ሁኔታ እንዳሉ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸውም ነግረውናል ብሏል።

እነዚህ ኦሮሞ በአርሲ የገደላቸው ኦርቶዶክሳውያን አማኞች የ9ኙ ስም ዝርዝር ነው
①አቶ ዘዉዴ ረዳ
② ወ/ሮ አታለሉ ንጋቱ
③ ለዝና ለገሠ
④ ብዙነሽ ለዝና
⑤ በላይነህ ጥላሁን
⑥ ተሾመ ስዩም
⑦ ዘላለም ተክለእሸት
⑧ ኃይሌ ወርቅነህ
⑨ አስቻለው ደለለኝ

መረጃን ከመሠረት!

1 Comment

  1. አባ ማትያስ ትግሬ ጠግቦ ሊጠብቀው የሄደውን ወታደር ሲያርድ ከቴዎድሮስ አድሀኖም ጋር ሁነው እሪታውን ያቀልጡታል ምእመኑ አማራ ከሆነ አይመለከታቸውም ያሳዝናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጮሌ ስልክና የማህበራዊ ግንኙነት ሜዳዎች ማይምነትን እያስፋፉ ነው!

Next Story

የሰብዓዊ ቀውስ በአማራ ክልል 6.1 ሚሊዮን ዜጎች የምግብ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው

Go toTop