አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አስገኘች

August 6, 2024
አትሌት ፅጌ ዱጉማ
ፅጌ ዱጉማ ለኢትዮጵያ በ800 ሜትር በታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አስገኘች
በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
የፅጌ ታሪክ በጥቂቱ
” አባቷን አታውቃቸውም፤ ገና በአንድ ዓመቷ ነው ያረፉት ከቤተሰቦቿ ሰባት ልጆች የመጨረሻዋ እሷ ነች አንድ ወንድም ብቻ ነው ያላት፤ ስድስቱ ሴቶች ናቸው በልጅነቷ አትሌቲክስ፣ እግር ኳስና ሌሎች ስፖርቶችን ታዘወትር ነበር በባዶ እግሯ መሮጥ ጀመረች፤ ትምህርት ቤት ስትሄድም በሩጫ ሆነ ወደደችው።
ብቸኛ ወንድሟ በሩጫው እንድትገፋ ያበረታታት ነበር ለትምህርት ቤት፣ ለወረዳ፣ ለዞንና ለክልል በአጭር ርቀቶች መሳተፍ ጀመረች ሁሉም እህቶቿ ትዳር መስርተው ከቤት ስለወጡ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር ወንድሟ አቅሟን ተመልክቶ አካዳሚ እንድትገባ ገፋፋት፤ እሷ ግን እናቴን ትቼ አልሄድም አለች ካልሄድሽማ እንጣላለን ብሎ አስጠነቀቃት በመጨረሻ ተስማማችና የትውልድ ቀዬዋን ለቀቀች።
አሰላ ጥሩነሽ ዲባባ ማዕከል የመግባት እድል አገኘች፤ የ100 እና 200 ሜትር ሯጭ ሆና አካዳሚውን ተቀላቀለች። ከሰባት አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገርን የመወከል እድል አገኘች በአፍሪካ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና በ200 ሜትር አልጄሪያ ላይ ተወዳደረች፤ የብር ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች ለአምስት አመት ያህል ከ100 እስከ 400 ሜትር ሮጠች ከባለፈው አንድ አመት ጀምሮ 800 ሜትር ላይ አተኮረች የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ሆነች አምና ቤልጂየም ላይ ለአለም ሻምፒዮና የሚያበቃት ሚኒማ አመጣች የዶፒንግ ምርመራ ወቅት በማለፉ ግን በቡዳፔስቱ የአለም ሻምፒዮና ሳትሳተፍ ቀረች በዚህ አመት በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ800 ሜትር አሸነፈች በአፍሪካ ሻምፒዮናም በተመሳሳይ ወርቅ አጠለቀች በኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሯን ወከለች ሁለቱን ማጣሪያዎች በብቃት አልፋ ለፍፃሜው በቃች።
እናም ዛሬ ምሽት…!
\የአቶ ዱጉማ ገመቹና የወይዘሮ ሜታ ሙለታ የመጨረሻ ልጅ የሆነችው፥ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሽ ተነስታ ፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ የተገኘችው፥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቷ፥ የ23 አመቷ ፅጌ ዱጉማ አዲስ ታሪክ ፅፋለች፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የሴቶች 800 ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ሀገሯን ከፍ አድርጋለች፤ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ርቀት ኢትዮጵያ ሜዳሊያ ውስጥ ገብታለች፤ የራሷን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች፤ 1:57:15፥
(አበባየሁ ተመስገን)
Previous Story

” የዐቢይ አህመድ ተሿሚ ሆኜ ሕዝቡን በመበደሌ ከልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ::”ገዱ አንዳርጋቸው

Next Story

የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ | የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

Latest from Same Tags

የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ | የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

https://youtu.be/GMjaXoaAvho?si=JHLNavMjxMse3KFg https://youtu.be/zsnYsJHwmfg?si=MZnzCl3JpShe5ByK የባህርዳር ውጥረት – ምን ተፈጠረ? | የአማራ ፋኖ በጎንደር አርበኛ ባዩ ቀናው መግለጫ አወጡ |  ገዱ አንዳርጋቸው ፋኖን ተቀላቀሉ

የምን መነሻ! የምን መድረሻ!

አንዱ ዓለም ተፈራ አርብ፣ ሐምሌ ፳ ፮ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ፮ ዓ. ም. (8/2/2024) በማንኛውም መነፅር ቢመለከቱት ወይንም ሚዛን ቢሰፍሩት፤ ዛሬ የዐማሮች ትግላችን አንድና አንድ ብቻ ነው! ነገን ለመኖር

ፊ/ማ ብርሃኑ ጁላ ለአብይ ቁርጡን ነገሩ | የሰራዊቱ አዛዥ በጄ/ል ተፈራ እጅ ወደቀ | ፋኖ ባልታሰበ ሁኔታ ወልድያ እና ደሴ ገባ | 4ተኛ ቀን ያስቆጠረው ከባዱ የጎንደር ትንቅንቅ

https://youtu.be/y2j-66loGR4?si=NPFS1BePQ3o8mVqJ የሰራዊቱ አዛዥ በጄ/ል ተፈራ እጅ ወደቀ | ፋኖ ባልታሰበ ሁኔታ ወልድያ እና ደሴ ገባ | 4ተኛ ቀን ያስቆጠረው ከባዱ የጎንደር ትንቅንቅ https://youtu.be/mYJGyCX07l4?si=nlqmoJ2gWiIYdF7J ፊ/ማ
Go toTop

Don't Miss