«ኮማንደር አሰግድ እጁን ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ ይቀለዋል» መሳይ መኮንን

July 22, 2024

ኮማንደር አሰግድ መኮንን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ የሚለው የብልጽግናው ዲጂታል ሰራዊትን ወሬ ለማጣራት የተወሰኑ ሙከራዎች አድርጌአለሁ። ማረጋገጫ ማገኘት አልቻልኩም። ሆኖም አንድ የሰሜን ሸዋ እዝ ከፍተኛ አመራር ሊሆን የማይችል የካድሬዎች ጫጫታ ነው የሚል መልስ ሰጠኝ።

ማታ በስልክ እንደተገናኙና በዚህ አጭር ሰዓታት ውስጥ ሊለወጥ የሚችል ተአምር እንደሌለም ነገሩኝ። ለጊዜው የኮማንደሩና አጠገቡ ያሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ዝግ በመሆኑ አሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ነገር ግን ”ኮማንደር አሰግድ እጅ ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ እንደሚመርጥ” በመግለጽ አመራሩ እርግጠኝነቱን አሳየኝ።
”ብዙ ጊዜ ኔትወርክ ስለማይኖር እንዲህ ዓይነት በስልክ አለመገናኘት የተለመደ እንደሆነና ዛሬ ምን ተፈጥሮ ወሬው እንደተዛመተ አላውቅም” በማለትም አብራራልኝ። ወደኋላ ላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ነግሮኝ ተለያየን።

እንግዲህ ስለጉዳዩ የማሳመን ሸክሙ የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት ላይ ወድቋል። ያዝን፡ እጁን ሰጠን ካሉ ያቅርቡና ያሳዩን። በተረፈ ቢሆንም ባይሆንም ትግል ነውና ትግሉ ይቀጥላል። ግለሰቦች በትግሉ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖራቸውና ያለመኖራቸው ተጽዕኖ ለህልወና ሲባል በተጀመረ ትግል ላይ የሚፈጥረው ኪሳራ ኢምንት ነው። የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ግለሰቦች አላስጀመሩትም።

ግለሰቦችም አያስቆሙትም። የጥቂት ቀናት ወሬ ሆኖ ይጠፋል። ትግል ይቀጥላል። ብልጽግናዎች ከበሮ መደለቁን በልኩ አድርጉት። ደረት መድቃትም ይኖራልና።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

4 ኪሎን ያስጨነቀው የጄ/ል ተፈራ ጦር | “ፋኖ እኛን ሳይጨ-ርስ 4 ኪሎ አይገባም” ሽመልስ

Next Story

እስክንድር ነጋ ይብቃው፣ ገለል ይበል

Go toTop